1 ጴጥሮስ 4:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያለ ማንጐራጐር እርስ በርሳችሁ እንግድነትን ተቀባበሉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርስ በርሳችሁ ያለ ማጕረምረም እንግድነት ተቀባበሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያለ ማጉረምረም እርስ በርሳችሁ በእንግድነትን ተቀባበሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያለ ማጒረምረም እርስ በርሳችሁ በእንግድነት ተቀባበሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያለ ማንጐራጐር እርስ በርሳችሁ እንግድነትን ተቀባበሉ፤ |
እኔንና አብያተ ክርስቲያናትን ሁሉ በእንግድነት የተቀበለ ጋይዮስም ሰላም ብሎአችኋል፤ የከተማው መጋቢ አርስጦስና ወንድማችን ቁአስጥሮስም ሰላም ብለዋችኋል።
እንግዲህ ኤጲስ ቆጶስ እንዲህ ሊሆን ይገባዋል፤ የማይነቀፍ፥ የአንዲት ሚስት ባል፥ ልከኛ፥ ራሱን የሚገዛ፥ እንደሚገባው የሚሠራ፥ እንግዳ ተቀባይ፥ ለማስተማር የሚበቃ፥
ነገር ግን ለድሆች መራራትን፥ ከእነርሱም ጋር መተባበርን አትርሱ፤ እንዲህ ያለው መሥዋዕት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋልና።