1 ነገሥት 9:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የፈርዖንንም ልጅ ከዳዊት ከተማ ሰሎሞን ወደ ሠራላት ወደ ቤቷ አመጣት፤ በዚያ ጊዜም ሚሎንን ሠራት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የፈርዖን ልጅ ከዳዊት ከተማ ሰሎሞን ወዳሠራላት ቤተ መንግሥት ከመጣች በኋላ ሰሎሞን ሚሎንን ሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የግብጽ ንጉሥ ልጅ የነበረችው ሚስቱ ከዳዊት ከተማ ራሱ ወዳሠራላት ቤተ መንግሥት ከተዘዋወረች በኋላ ሰሎሞን ከከተማይቱ በስተ ምሥራቅ የሚገኘውን ጐድጓዳ ስፍራ ተሞልቶ በመስተካከል እንዲሠራ አደረገ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የግብጽ ንጉሥ ልጅ የነበረችው ሚስቱ ከዳዊት ከተማ ራሱ ወዳሠራላት ቤተ መንግሥት ከተዘዋወረች በኋላ ሰሎሞን ከከተማይቱ በስተ ምሥራቅ የሚገኘውን ጐድጓዳ ስፍራ ተሞልቶ በመስተካከል እንዲሠራ አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የፈርዖንም ልጅ ከዳዊት ከተማ ሰሎሞን ወደ ሠራላት ወደ ቤትዋ ወጣች፤ በዚያን ጊዜም ሚሎን ሠራ። |
ዳዊትም በአንባዪቱ ውስጥ ተቀመጠ፤ እርስዋም የዳዊት ከተማ ተባለች። ከተማዋንም ዙሪያዋን እስከ ዳርቻዋ ድረስ ቀጠራት፤ ቤቱንም ሠራ።
እርሱም ያደረገው ይህ ነው በንጉሡ በሰሎሞን ላይ እጁን አነሣ፤ ሰሎሞንም በዳርቻ ያለ ቅጥርንና የአባቱን የዳዊትን ከተማ ቅጥር ሠርቶ ጨረሰ።
ሰሎሞንም ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖን አማች ሆነ፤ የፈርዖንንም ልጅ አገባ፤ ቤቱንና የእግዚአብሔርንም ቤት፥ በኢየሩሳሌምም ዙሪያ ያለውን ቅጥር ሠርቶ እስኪፈጽም ድረስ ወደ ዳዊት ከተማ አምጥቶ አስገባት።
ከፍርድ ሰቀላ ወደ ውስጥ፥ በሌላውም አደባባይ ውስጥ የነበረውን የሚኖርበትን ቤት እንዲሁ ሠራ፤ እንደዚህም ቤት ያለ ቤትን ሰሎሞን ላገባት ለፈርዖን ልጅ ሠራ።
ሕዝቅያስም ሰውነቱን አጽናና፤ የፈረሰውንም ቅጥር ሁሉ ጠገነ፤ በላዩም ግንብ ሠራበት፤ ከእርሱም በስተውጭ ሌላ ቅጥር ሠራ፤ ወደ ዳዊትም ከተማ የሚያወጣውን በር አጠነከረ፤ ብዙም መሣሪያና ጋሻ አዘጋጀ።
ሰሎሞንም፥ “የእግዚአብሔር ታቦት የገባችበት ስፍራ ቅዱስ ነውና ሚስቴ በእስራኤል ንጉሥ በዳዊት ቤት አትቀመጥም” ሲል የፈርዖንን ልጅ ከዳዊት ከተማ ወደ ሠራላት ቤት አወጣት።