1 ነገሥት 9:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰሎሞንም በሚሠራው ሥራ ላይ ሠራተኛውን ሕዝብ የሚያዝዙ አለቆች አምስት መቶ አምሳ ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህም ሰሎሞን የሚያሠራውን ሥራ የሚያከናውኑትን ሠራተኞች የሚቈጣጠሩ አለቆች ናቸው፤ ቍጥራቸውም ዐምስት መቶ ዐምሳ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰሎሞን ለሚያከናውነው የሕንጻ ሥራ የጉልበት ሥራ ይሠሩ ዘንድ ለተመደቡት ሰዎች አምስት መቶ ኀምሳ ኀላፊዎች ነበሩአቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰሎሞን ለሚያከናውነው የሕንጻ ሥራ የጒልበት ሥራ ይሠሩ ዘንድ ለተመደቡት ሰዎች አምስት መቶ ኀምሳ ኀላፊዎች ነበሩአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰሎሞንም በሚሠራው ሥራ ላይ ሠራተኛውን ሕዝብ የሚያዝዙ አለቆች አምስት መቶ አምሳ ነበሩ። |
ከእነርሱም የሚሸከሙትን ሰባ ሺህ፥ በተራሮቹም ላይ የሚጠርቡትን ሰማንያ ሺህ፥ በሕዝቡም ሥራ ላይ የተሾሙትን ሦስት ሺህ ስድስት መቶ አደረገ።