ሰሎሞንም ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖን አማች ሆነ፤ የፈርዖንንም ልጅ አገባ፤ ቤቱንና የእግዚአብሔርንም ቤት፥ በኢየሩሳሌምም ዙሪያ ያለውን ቅጥር ሠርቶ እስኪፈጽም ድረስ ወደ ዳዊት ከተማ አምጥቶ አስገባት።
1 ነገሥት 9:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰሎሞንም የእግዚአብሔርን ቤትና የንጉሡን ቤት ሁለቱን ቤቶች በሠራበት በሃያ ዓመት ውስጥ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰሎሞን ሁለቱን ሕንጻዎች፣ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስና የንጉሡን ቤተ መንግሥት ሠርቶ በፈጸመበት በሃያኛው ዓመት መጨረሻ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰሎሞን ቤተ መቅደሱንና ቤተ መንግሥቱን ለመሥራት የፈጀበት ጊዜ ኻያ ዓመት ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰሎሞን ቤተ መቅደሱንና ቤተ መንግሥቱን ለመሥራት የፈጀበት ጊዜ ኻያ ዓመት ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰሎሞንም የእግዚአብሔርን ቤትና የንጉሡን ቤት ሁለቱን ቤቶች የሠራበት ሃያ ዓመት በተፈጸመ ጊዜ፥ |
ሰሎሞንም ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖን አማች ሆነ፤ የፈርዖንንም ልጅ አገባ፤ ቤቱንና የእግዚአብሔርንም ቤት፥ በኢየሩሳሌምም ዙሪያ ያለውን ቅጥር ሠርቶ እስኪፈጽም ድረስ ወደ ዳዊት ከተማ አምጥቶ አስገባት።
በዐሥራ አንደኛውም ዓመት ቡል በሚባል በስምንተኛው ወር ቤቱ እንደ ክፍሎቹና እንደ ሥርዐቱ ሁሉ ተጨረሰ። በሰባት ዓመትም ሠራው።
ከዚህም በኋላ ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤት፥ የንጉሡን ቤትና ሰሎሞን ያደርገው ዘንድ የወደደውን ሁሉ ሠርቶ በፈጸመ ጊዜ፥
የጢሮስ ንጉሥ ኪራም በዝግባና በጥድ እንጨት፥ በወርቅና በሚሻውም ሁሉ ሰሎሞንን ረድቶት ነበር። ያንጊዜም ንጉሡ ሰሎሞን በገሊላ ምድር ያሉትን ሃያ ከተሞች ለኪራም ሰጠው።
እንደዚህም ብለው መለሱልን፦ እኛ የሰማይና የምድር አምላክ ባሪያዎች ነን፥ ከብዙም ዘመን ጀምሮ ተሠርቶ የነበረውን፥ ታላቁም የእስራኤል ንጉሥ ሠርቶ ፈጽሞላቸው የነበረውን ቤት እንሠራለን።