በሁለቱም አዕማድ ራስ ላይ እንዲቀመጡ ከፈሰሰ ናስ ሁለት ጕልላትን ሠራ፤ የአንዱም ጕልላት ቁመት አምስት ክንድ፥ የሁለተኛውም ጕልላት ቁመት አምስት ክንድ ነበረ።
1 ነገሥት 7:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቤቱ ውስጥ ላለው ወለል ሁለቱን የናስ አዕማድ ሠራ፤ የአንዱም ዓምድ ቁመት ዐሥራ ስምንት ክንድ ነበረ፤ የዙሪያውም መጠን ዐሥራ ሁለት ክንድ ነበረ፤ የዓምዱም ውፍረት አንድ ጋት ነበረ፤ ውስጠ ክፍትም ነበረ። ሁለተኛውም ዓምድ እንዲሁ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኪራም የእያንዳንዱ ቁመት ዐሥራ ስምንት ክንድ፣ ዙሪያው ዐሥራ ሁለት ክንድ የሆነ፣ ሁለት የናስ ምሰሶዎች ሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሑራም የእያንዳንዳቸው ቁመት ስምንት ሜትር፥ የዙሪያ ስፋታቸው አምስት ሜትር ከሠላሳ ሳንቲ ሜትር ውስጡ ክፍት የሆነ አራት ጣት ውፍረት ካለው ነሐስ ሁለት ምሰሶዎችን ሠራ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሑራም የእያንዳንዳቸው ቁመት ስምንት ሜትር፥ የዙሪያ ስፋታቸው አምስት ሜትር ከሠላሳ ሳንቲ ሜትር ውስጡ ክፍት የሆነ አራት ጣት ውፍረት ካለው ነሐስ ሁለት ምሰሶዎችን ሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁለቱን የናስ አዕማድ አደረገ፤ የአንዱም ዐምድ ቁመት ዐሥራ ስምንት ክንድ ነበረ፤ የዙሪያውም መጠን ዐሥራ ሁለት ክንድ ነበረ፤ የዐምዱም ውፍረት አንድ ጋት ነበረ፤ ውስጠ ክፍትም ነበረ። ሁለተኛውም ዐምድ እንዲሁ ነበረ። |
በሁለቱም አዕማድ ራስ ላይ እንዲቀመጡ ከፈሰሰ ናስ ሁለት ጕልላትን ሠራ፤ የአንዱም ጕልላት ቁመት አምስት ክንድ፥ የሁለተኛውም ጕልላት ቁመት አምስት ክንድ ነበረ።
አዕማዱንም በመቅደሱ ወለል አጠገብ አቆማቸው፤ የቀኙንም ዓምድ አቁሞ ያቁም ብሎ ጠራው፤ የግራውንም ዓምድ አቁሞ በለዝ ብሎ ጠራው።
ሁለቱንም አዕማድ፥ በሁለቱም አዕማድ ራስ ላይ የነበሩትን ኩብ የሚመስሉትን ጕልላቶች፥ በሁለቱም አዕማድ ላይ የነበሩትን ሁለቱን ጕልላቶች የሚሸፍኑትን ሁለቱን መርበቦች፥
ከለዳውያንም በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የነበሩትን የናስ ዓምዶች፥ በእግዚአብሔርም ቤት የነበሩትን መቀመጫዎችና የናስ ኵሬዎች ሰባበሩ፤ ናሱንም ወደ ባቢሎን ወሰዱ።
ከሚጢብሐትና ከተመረጡት ከአድርአዛር ከተሞች ዳዊት እጅግ ብዙ ናስ ወሰደ፤ ከዚህም ሰሎሞን የናሱን ኩሬና ዓምዶች የናሱንም ዕቃ ሠራ።
ስላልወሰዳቸው ዓምዶች፥ ስለ ባሕሩም፥ ስለ መቀመጫዎቹም፥ በዚች ከተማ ስለ ቀሩት ዕቃዎች ሁሉ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦
የእግዚአብሔርን ቤትና የንጉሡን ቤት አቃጠለ፤ የኢየሩሳሌምንም ቤቶች ሁሉ ፥ ታላላቆችን ቤቶች ሁሉ፥ በእሳት አቃጠለ።
ከለዳውያንም በእግዚአብሔር ቤት የነበሩትን የናስ ዐምዶች በእግዚአብሔርም ቤት የነበሩትን መቀመጫዎችና የናሱን ኩሬ ሰባበሩ፤ ናሱንም ወደ ባቢሎን ወሰዱ።
ዐምዶቹም፥ የአንዱ ዓምድ ቁመት ዐሥራ ስምንት ክንድ ነበረ፥ የዙሪያውም መጠን ዐሥራ ሁለት ክንድ ነበረ፤ ውፍረቱም ጋት ያህል ነበረ፤ ባዶም ነበረ።
የደጀ ሰላሙም ርዝመት ሃያ ክንድ፥ ወርዱም ዐሥራ ሁለት ክንድ ነበረ፥ ወደ እርሱም የሚያደርሱ ዐሥር ደረጃዎች ነበሩ፤ አንድ በዚህ ወገን፥ አንድም በዚያ ወገን ሆነው በመቃኖቹ አጠገብ የግንብ አዕማድ ነበሩ።