የቤቱንም ውስጥ በተጐበጐበና በፈነዳ አበባ፥ በተቀረጸ ዝግባ ለበጠው፤ ሁሉም ዝግባ ነበረ፤ ድንጋዩም አልታየም ነበር።
1 ነገሥት 6:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁለቱንም ሣንቃዎች ከወይራ እንጨት ሠራ፤ የኪሩቤልንና የዘንባባ ዛፍ፥ የፈነዳም አበባ ሥዕል ቀረጸባቸው፤ በወርቅም ለበጣቸው፤ ኪሩቤልንና የዘንባባውን ዛፍ በወርቅ ለበጠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሁለቱ የወይራ ዕንጨት መዝጊያዎችም ላይ ኪሩቤልን፣ የዘንባባ ዛፎችንና የፈነዱ አበቦችን ቀረጸ፤ በወርቅም ለበጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁለቱን በሮች በኪሩቤል፥ በዘንባባ ዛፎችና በፈኩ የአበባ ቅርጾች አስጌጣቸው፤ እርሱም በሮቹን፥ ኪሩቤልን፥ የዘንባባ ዛፎቹን፥ ቅርጾቹንም በወርቅ ለበጣቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁለቱን በሮች በኪሩቤል፥ በዘንባባ ዛፎችና በፈኩ የአበባ ቅርጾች አስጌጣቸው፤ እርሱም በሮቹን፥ ኪሩቤልን፥ የዘንባባ ዛፎቹን፥ ቅርጾቹንም በወርቅ ለበጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁለቱንም ደጆች ከወይራ እንጨት ሠራ፤ የኪሩቤልንና የዘንባባ ዛፍ የፈነዳም አበባ ምስል ቀረጸባቸው፤ በወርቅም ለበጣቸው፤ ኪሩቤልንና የዘንባባውን ዛፍ በወርቅ ለበጣቸው። |
የቤቱንም ውስጥ በተጐበጐበና በፈነዳ አበባ፥ በተቀረጸ ዝግባ ለበጠው፤ ሁሉም ዝግባ ነበረ፤ ድንጋዩም አልታየም ነበር።
ለቅድስተ ቅዱሳኑም መግቢያ ከወይራ እንጨት ሳንቃዎችን ሠራ፤ መድረኩንና መቃኖቹን፥ ደፉንም አምስት ማዕዘን አደረገ።
ውስጠኛው የእግዚአብሔር ቤት ደጅና ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ መግቢያ የሚወስደው የውስጠኛውም የቤተ መቅደሱ ደጆች የወርቅ ነበሩ። እንዲሁም ሰሎሞን ስለ እግዚአብሔር ቤት የሠራው ሥራ ሁሉ ተፈጸመ።
በዕቃ ቤቶቹም በበሩ ውስጥ በዙሪያው በነበሩትም በግንቡ አዕማድ የዐይነ ርግብ መስኮቶች ነበሩባቸው፤ ደግሞም በደጀ ሰላሙ ውስጥ በዙሪያው መስኮቶች ነበሩ፤ በግንቡም አዕማድ ሁሉ ላይ የዘንባባ ዛፍ ተቀርጾባቸው ነበር።
ኪሩቤልና የዘንባባው ዛፎች ተቀርጸውበት ነበር፤ የዘንባባውም ዛፍ ከኪሩብና ከኪሩብ መካከል ነበረ፤ ለእያንዳዱም ኪሩብ ሁለት ፊት ነበረው።