1 ነገሥት 5:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይኸውም በሰሎሞን ሥራ ላይ ከተሾሙት ከሦስት ሺህ ስድስት መቶ የሠራተኞች አለቆች ሌላ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ሰሎሞን ሥራውን የሚቈጣጠሩ ሦስት ሺሕ ሦስት መቶ ኀላፊዎች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእነዚህ ሠራተኞች የበላይ ሆነው ሥራውን የሚቆጣጠሩ ሦስት ሺህ ሦስት መቶ ሰዎችን አዘጋጀ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእነዚህ ሠራተኞች የበላይ ሆነው ሥራውን የሚቈጣጠሩ ሦስት ሺህ ሦስት መቶ ሰዎችን አዘጋጀ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይኸውም በሠራተኛው ሕዝብ ላይ ከተሾሙት ከሦስት ሺህ ስድስት መቶ ሰዎች ሌላ ነው። |
ሰሎሞንም የሚሸከሙትን ሰባ ሺህ፥ ከተራሮችም ድንጋዮችን የሚጠርቡትን ሰማንያ ሺህ፥ በእነርሱም ላይ የተሾሙትን ሦስት ሺህ ስድስት መቶ ሰዎች ሰበሰበ።