ድንበሩም ከበኣላ በባሕር በኩል ያልፋል፤ ከዚያም በኢያሪም ከተማ ደቡብ በኩልና በኪስሎን ሰሜን በኩል ወደ አሥራቱስ ድንበር ያልፋል፤ በፀሐይ ከተማም ላይ ይወርዳል፤ በሊባም በኩል ያልፋል።
1 ነገሥት 4:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በማኪስና በሰአልቢን፥ በቤት ሳሚስና በኤሎንቤትሐናን የዴቀር ልጅ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቤንጼቄር፣ በማቃጽ፣ በሻዓልቢም፣ በቤትሳሚስ፣ በኤሎንቤትሐናን፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቤንዴቀር፦ የማቃጽ፥ የሻዓልቢም፥ የቤትሼሜሽ፥ የኤሎንና የቤት ሐናን ከተሞች ገዥ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቤንዴቀር፦ የማቃጽ፥ የሻዓልቢም፥ የቤትሼሜሽ፥ የኤሎንና የቤት ሐናን ከተሞች ገዥ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በማቃጽና በሸዓልቢም በቤትሳሚስና በኤሎንቤትሐና የዴቀር ልጅ፤ |
ድንበሩም ከበኣላ በባሕር በኩል ያልፋል፤ ከዚያም በኢያሪም ከተማ ደቡብ በኩልና በኪስሎን ሰሜን በኩል ወደ አሥራቱስ ድንበር ያልፋል፤ በፀሐይ ከተማም ላይ ይወርዳል፤ በሊባም በኩል ያልፋል።
አሳንና መሰማርያዋን፥ ዮጣንንና መሰማርያዋን፥ ቤትሳሚስንና መሰማርያዋን፤ ከእነዚህ ከሁለቱ ነገዶች ዘጠኝ ከተሞችን ሰጡ።
አሞሬዎናውያንም ድብና ቀበሮዎች በሚኖሩበት በመርስኖኖስ ተራራ መቀመጥ ጀመሩ፤ ነገር ግን የዮሴፍ ወገን እጅ በአሞሬዎናውያን ላይ ጸናች፤ ገባርም አደረጉአቸው።
ላሞችም ወደ ቤትሳሚስ ወደሚወስደው መንገድ አቅንተው “እምቧ” እያሉ በጎዳናው ላይ ሄዱ፤ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አላሉም፤ የፍልስጥኤማውያን አለቆችም እስከ ቤትሳሚስ ዳርቻ ድረስ በኋላ በኋላ ይሄዱ ነበር።
የቤትሳሚስም ሰዎች፥ “በዚህ በቅዱሱ አምላክ በእግዚአብሔር ፊት ማለፍ ማን ይችላል? የእግዚአብሔር ታቦት ከእኛ ወጥታ ወደ ማን ትሄዳለች?” አሉ።
ወደምትሄድበትም ተመልከቱ፤ በድንበሩም መንገድ ላይ ወደ ቤትሳሚስ ብትወጣ ይህን እጅግ ክፉ ነገር ያደረገብን እርሱ ነው፤ አለዚያም እንዲያው መጥቶብናል እንጂ የመታን የእርሱ እጅ እንዳልሆነ እናውቃለን።”