ኢዮአብም በእስራኤል ሠራዊት ሁሉ ላይ አለቃ ነበረ፤ የዮዳሄም ልጅ በናያስ በከሊታውያንና በፈሊታውያን ላይ አለቃ ነበረ፤
1 ነገሥት 4:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጸሓፊዎቹም የሱባ ልጆች ኤልያብና አኪያ፥ ታሪክ ጸሓፊውም የአሒሉድ ልጅ ኢዮሣፍጥ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሺሻ ልጆች ኤሊሖሬፍና አኪያ፣ ጸሓፊዎች፤ የአሒሉድ ልጅ ኢዮሣፍጥ፣ ታሪክ ጸሓፊ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤሊሖሬፍና አኪያ የተባሉት የሺሻ ልጆች፥ የቤተ መንግሥት ጸሐፊዎች፤ ኢዮሣፍጥ የተባለው የአሒሉድ ልጅ፥ ታሪክ ጸሐፊና የመዛግብት ኀላፊ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኤሊሖሬፍና አኪያ የተባሉት የሺሻ ልጆች፥ የቤተ መንግሥት ጸሐፊዎች፤ ኢዮሣፍጥ የተባለው የአሒሉድ ልጅ፥ ታሪክ ጸሐፊና የመዛግብት ኀላፊ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጸሐፊዎቹም የሴባ ልጆች ኤልያፍና አኪያ፥ ታሪክ ጸሐፊም የአሒሉድ ልጅ ኢዮሣፍጥ፥ |
ኢዮአብም በእስራኤል ሠራዊት ሁሉ ላይ አለቃ ነበረ፤ የዮዳሄም ልጅ በናያስ በከሊታውያንና በፈሊታውያን ላይ አለቃ ነበረ፤
ዳዊትም በደማስቆ ሶርያ ጭፍሮችን አኖረ፤ ሶርያውያንም ለዳዊት ገባሮች ሆኑ፤ ግብርም አመጡለት። እግዚአብሔርም ዳዊትን በሄደበት ሁሉ ያድነው ነበር።
ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ጠባቂዎችሽን በቅጥርሽ ላይ ቀንና ሌሊት አቁሜአለሁ፤ እግዚአብሔርን የሚያስቡ ከቶ ዝም አይሉም፤
የዔሊ ልጅ፥ የፊንሐስ ልጅ፥ የዮካብድ ወንድም፥ የአኪጦብ ልጅ በሴሎ ለእግዚአብሔር ካህን የሆነ፥ ኤፉድም የለበሰ አኪያ አብሮ ነበር፤ ሕዝቡም ዮናታን እንደ ሄደ አላወቁም ነበር።