ከዚህም በኋላ ዳዊት ሰማ፤ እንዲህም አለ፥ “ከኔር ልጅ ከአበኔር ደም በእግዚአብሔር ዘንድ ለዘለዓለም እኔ ንጹሕ ነኝ፤ መንግሥቴም ንጹሕ ነው፤
1 ነገሥት 2:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም አለው፥ “ሂድና እንደ ነገረህ አድርግ፤ ገድለህም ቅበረው፤ ኢዮአብም በከንቱ ያፈሰሰውን ደም ከእኔና ከአባቴ ቤት ታርቃለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡም በናያስን እንዲህ ሲል አዘዘው፤ “በል እንዳለው አድርግ፤ ግደልና ቅበረው፤ ኢዮአብ በከንቱ ካፈሰሰው ንጹሕ ደምም እኔንና የአባቴን ቤት አንጻን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰሎሞንም በናያን እንዲህ አለው፤ “ኢዮአብ እንዳለህ ግደለውና ቅበረው፤ በዚህ አኳኋን ኢዮአብ ካፈሰሰው ንጹሕ ደም በደል የእኔንና የአባቴን ቤት የነጻን አድርገን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰሎሞንም በናያን እንዲህ አለው፦ “ኢዮአብ እንዳለህ ግደለውና ቅበረው፤ በዚህ አኳኋን ኢዮአብ ካፈሰሰው ንጹሕ ደም በደል የእኔንና የአባቴን ቤት የነጻን አድርገን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም አለው “እንደ ነገረህ አድርግ፤ ኢዮአብም በከንቱ ያፈሰሰውን ደም ከእኔና ከአባቴ ቤት ታርቅ ዘንድ ገድለህ ቅበረው። |
ከዚህም በኋላ ዳዊት ሰማ፤ እንዲህም አለ፥ “ከኔር ልጅ ከአበኔር ደም በእግዚአብሔር ዘንድ ለዘለዓለም እኔ ንጹሕ ነኝ፤ መንግሥቴም ንጹሕ ነው፤
በኢዮአብ ራስ ላይና በአባቱ ቤት ሁሉ ላይ ይምጣበት፤ በኢዮአብም ቤት ፈሳሽ ነገር ያለበት ወይም ለምጻም ወይም አንካሳ ወይም በሰይፍ የሚወድቅ ወይም እንጀራ የሌለው ሰው አይታጣ።”
የዮዳሄ ልጅ በንያስም ወደ ኢዮአብ ወደ እግዚአብሔር ድንኳን መጥቶ፥ “ንጉሡ፦ ውጣ ይልሃል” አለው፤ ኢዮአብም፥ “በዚህ እሞታለሁ እንጂ አልወጣም” አለ። የዮዳሄ ልጅ በንያስም፦ ተመልሶ “ኢዮአብ የተናገረው ቃል፥ የመለሰልኝም እንዲህ ነው” ብሎ ለንጉሡ ነገረው።
በእውነት የናቡቴንና የልጆቹን ደም ትናንትና አይቻለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በዚህም እርሻ እበቀለዋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር። ስለዚህ እግዚአብሔር እንደ ተናገረው ቃል ወስደህ በእርሻው ውስጥ ጣለው።”
ምድርን የሚያረክሳት ደም ነውና የምትኖሩባትን ምድር በነፍስ ግድያ አታርክሷት። ምድሪቱም በደም አፍሳሹ ደም ካልሆነ በቀር ከፈሰሰባት ደም አትነጻም።
አረማውያንም እፉኝቱ በጳውሎስ እጅ ላይ ተንጠልጥላ ባዩ ጊዜ እርስ በርሳቸው፥ “ይህ ሰው ነፍሰ ገዳይ ይመስላል፤ ከባሕር እንኳ በደኅና ቢወጣም በሕይወት ይኖር ዘንድ የእግዚአብሔር ፍርድ አልተወውም” አሉ።