La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ነገሥት 19:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እር​ሱም አንድ ቀን የሚ​ያ​ህል መን​ገድ በም​ድረ በዳ ሄደ፤ መጥ​ቶም ከደ​ድሆ ዛፍ በታች ተቀ​መ​ጠና፦ ይበ​ቃ​ኛል፤ አሁ​ንም አቤቱ! እኔ ከአ​ባ​ቶቼ አል​በ​ል​ጥ​ምና ነፍ​ሴን ውሰድ” ብሎ እን​ዲ​ሞት ለመነ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በምድረ በዳም ውስጥ የአንድ ቀን መንገድ ተጓዘ፤ ወደ አንድ ክትክታ ዛፍ እንደ መጣም፣ ከሥሩ ተቀምጦ፣ ይሞት ዘንድ “እግዚአብሔር ሆይ፤ በቅቶኛል፤ እኔ ከቀደሙት አባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰዳት” ብሎ ጸለየ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኤልያስ አንድ ቀን ሙሉ በበረሓ ተጓዘ፤ ከዚህ በኋላ ጉዞውን ቆም አድርጎ፥ በአንድ የክትክታ ዛፍ ጥላ ሥር ተቀመጠ፤ ሞቱንም በመመኘት “ጌታ ሆይ! አሁንስ ይብቃኝ፤ ከቀድሞ አባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰድ!” ሲል ጸለየ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኤልያስ አንድ ቀን ሙሉ በበረሓ ተጓዘ፤ ከዚህ በኋላ ጒዞውን ቆም አድርጎ፥ በአንድ የክትክታ ዛፍ ጥላ ሥር ተቀመጠ፤ ሞቱንም በመመኘት “እግዚአብሔር ሆይ! አሁንስ ይብቃኝ፤ ከቀድሞ አባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰድ!” ሲል ጸለየ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እርሱም አንድ ቀን የሚያህል መንገድ በምድረ በዳ ሄደ፤ መጥቶም ከክትክታ ዛፍ በታች ተቀመጠና “ይበቃኛል፤ አሁንም፥ አቤቱ፥ እኔ ከአባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰድ፤” ብሎ እንዲሞት ለመነ።

Ver Capítulo



1 ነገሥት 19:4
19 Referencias Cruzadas  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሰው ተከ​ት​ሎት ሄደ፤ ከዛፍ በታ​ችም ተቀ​ምጦ አገ​ኘ​ውና፥ “ከይ​ሁዳ የመ​ጣህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው አንተ ነህን?” አለው። እር​ሱም፥ “አዎ፥ እኔ ነኝ” አለ።


ኤል​ያ​ስም ፈርቶ ተነሣ፤ ነፍ​ሱ​ንም ሊያ​ድን ሄደ፤ በይ​ሁ​ዳም ወዳ​ለው ወደ ቤር​ሳ​ቤህ መጥቶ ብላ​ቴ​ና​ውን በዚያ ተወ።


በደ​ድ​ሆ​ውም ዛፍ በታች ተኛ፤ እን​ቅ​ል​ፍም አን​ቀ​ላፋ፤ እነ​ሆም፥ መል​አክ ዳሰ​ሰ​ውና፥ “ተነ​ሥ​ተህ ብላ” አለው።


ሁለ​ቱም እየ​ተ​ነ​ጋ​ገሩ ሲሄዱ፥ እነሆ፥ የእ​ሳት ሰረ​ገ​ላና የእ​ሳት ፈረ​ሶች በሁ​ለቱ መካ​ከል ገብ​ተው ከፈ​ሉ​አ​ቸው፤ ኤል​ያ​ስም በዐ​ውሎ ነፋስ ንው​ጽ​ው​ጽታ ወደ ሰማይ ወጣ።


ልመ​ናዬ ምነው በደ​ረ​ሰ​ልኝ! እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተስ​ፋ​ዬን ምነው በሰ​ጠኝ!


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያቈ​ስ​ለኝ ዘንድ ጀመረ፥ ነገር ግን እስከ መጨ​ረ​ሻው አላ​ጠ​ፋ​ኝም።


እኔም እን​ዲህ አልሁ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም አላ​ነ​ሣም፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ በስሙ አል​ና​ገ​ርም፥” በአ​ጥ​ን​ቶች ውስጥ እንደ ገባ እን​ደ​ሚ​ነ​ድድ እሳት ያለ በልቤ ሆነ​ብኝ፤ ደከ​ምሁ፤ መሸ​ከ​ምም አል​ቻ​ል​ሁም።


የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ፥ ወደ ካልኔ ተሻ​ግ​ራ​ችሁ ተመ​ል​ከቱ፤ ከዚ​ያም ወደ ኤማ​ት​ራባ እለፉ፤ ከዚ​ያም ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤም ጌት ውረዱ፤ እነ​ርሱ ከእ​ነ​ዚህ መን​ግ​ሥ​ታት ይበ​ረ​ታሉ፤ ድን​በ​ራ​ቸ​ውም ከድ​ን​በ​ራ​ቸው ይሰ​ፋ​ልና።


አሁ​ንም አቤቱ! ከሕ​ይ​ወት ሞት ይሻ​ለ​ኛ​ልና እባ​ክህ! ነፍ​ሴን ከእኔ ውሰድ።”


ፀሐ​ይም በወ​ጣች ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትኩስ የም​ሥ​ራቅ ነፋ​ስን አዘዘ፤ ዮና​ስ​ንም እስ​ኪ​ዝል ድረስ ፀሐይ ራሱን መታው፤ ለራ​ሱም ተስፋ ቈርጦ፥ “ከሕ​ይ​ወት ሞት ይሻ​ለ​ኛል” አለ።


አንቺ በመስኖች መካከል ከተቀመጠችው፥ ውኃም በዙሪያዋ ከነበራት፥ ምሽግዋም ባሕር ከነበረ፥ ቅጥርዋም በባሕር ውስጥ ከነበረ ከኖእ አሞን ትበልጫለሽን?


እን​ዲ​ህስ ከም​ታ​ደ​ር​ግ​ብኝ፥ በፊ​ትህ ይቅ​ር​ታን አግ​ኝቼ እንደ ሆነ፥ በእኔ ላይ የሚ​ሆ​ነ​ውን መከራ እን​ዳ​ላይ፥ እባ​ክህ፥ ፈጽሞ ግደ​ለኝ።”


ወደ ሰማይ ወፎች ተመልከቱ፤ አይዘሩም አያጭዱምም በጎተራም አይከቱም፤ የሰማዩ አባታችሁም ይመግባቸዋል፤ እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን?


በዚ​ያም የያ​ዕ​ቆብ የውኃ ጕድ​ጓድ ነበረ። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መን​ገድ በመ​ሄድ ደክሞ በዚያ ጕድ​ጓድ አጠ​ገብ ተቀ​መጠ፤ ጊዜ​ውም ስድ​ስት ሰዓት ያህል ነበር።


እን​ግ​ዲህ ምን እን​ላ​ለን? ከእ​ነ​ርሱ እን​በ​ል​ጣ​ለን? አይ​ደ​ለም፤ አይ​ሁ​ዳ​ዊ​ንም፥ አረ​ማ​ዊ​ንም እነሆ፥ አስ​ቀ​ድ​መን ነቅ​ፈ​ና​ቸ​ዋል፤ ሁሉም ስተ​ዋ​ልና።