ሄዶም፥ ሬሳው በመንገድ ወድቆ፥ በሬሳውም አጠገብ አህያውና አንበሳው ቆመው፥ አንበሳውም ሬሳውን ሳይበላው፥ አህያውንም ሳይሰብረው አገኘ።
1 ነገሥት 17:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከፈፋው ትጠጣለህ፤ ቁራዎችም በዚያ ይመግቡህ ዘንድ አዝዣለሁ።” ሄደም፥ እግዚአብሔርም እንዳዘዘው አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ውሃ ከወንዙ ትጠጣለህ፤ ቍራዎችም እዚያው እንዲመግቡህ አዝዣለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምትጠጣውንም ውሃ ከዚያው ወንዝ ታገኛለህ፤ ቁራዎችም ምግብ እንዲያመጡልህ አዝዣለሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምትጠጣውንም ውሃ ከዚያው ወንዝ ታገኛለህ፤ ቊራዎችም ምግብ እንዲያመጡልህ አዝዣለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከወንዙም ትጠጣለህ፤ ቍራዎችም በዚያ ይመግቡህ ዘንድ አዝዣለሁ።” |
ሄዶም፥ ሬሳው በመንገድ ወድቆ፥ በሬሳውም አጠገብ አህያውና አንበሳው ቆመው፥ አንበሳውም ሬሳውን ሳይበላው፥ አህያውንም ሳይሰብረው አገኘ።
“ተነሥተህ በሲዶና አጠገብ ወዳለችው ወደ ሰራፕታ ሂድ፤ በዚያም ተቀመጥ፤ እነሆም፥ ትመግብህ ዘንድ አንዲት መበለት አዝዣለሁ።”
እግዚአብሔርም ዮናስን ይውጠው ዘንድ ታላቅ ዓሣ አንበሪን አዘዘ፤ ዮናስም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በዓሣ አንበሪው ሆድ ውስጥ ነበረ።
“ይህችን በትርህን ውሰድ፤ አንተና ወንድምህ አሮንም ማኅበሩን ሰብስቡ፤ ዐለቷንም በፊታቸው እዘዟት፤ ውኃ ትሰጣለች፤ ከድንጋይዋም ውኃ ታወጡላቸዋላችሁ፤ እንዲሁም ማኅበሩን፥ ከብቶቻቸውንም ታጠጡላቸዋላችሁ።”