በዚያችም ሌሊት እግዚአብሔር ተገለጠለት፤ እንዲህም አለው፥ “እኔ የአባትህ የአብርሃም አምላክ ነኝ፤ አትፍራ፤ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና፤ እባርክሃለሁ፤ ስለ አባትህ ስለ አብርሃም ዘርህን አበዛዋለሁ።”
1 ነገሥት 17:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤልያስም አላት፥ “በእግዚአብሔር እመኚ፤ አትፍሪ፤ ሄደሽም እንዳልሽው አድርጊ፤ አስቀድመሽ ግን ከዱቄቱ ለእኔ ታናሽ እንጎቻ አድርገሽ አምጭልኝ፥ ከዚያም በኋላ ለአንቺና ለልጅሽ አድርጊ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤልያስም መልሶ እንዲህ አላት፤ “አይዞሽ አትፍሪ፤ ወደ ቤት ገብተሽ እንዳልሽው አድርጊ፤ በመጀመሪያ ግን ከዚያችው ካለችሽ ትንሽ ዕንጐቻ ጋግረሽ አምጪልኝ፤ ከዚያም ለራስሽና ለልጅሽ ጋግሪ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤልያስም እንዲህ አላት፤ “አይዞሽ አትጨነቂ! ሄደሽ ምግብሽን አዘጋጂ፤ አስቀድመሽ ግን ከዚያችው ካለችሽ ዱቄት ለእኔ ትንሽ እንጐቻ ጋግረሽ አምጪልኝ፤ የቀረውንም ለራስሽና ለልጅሽ ጋግሪው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኤልያስም እንዲህ አላት፤ “አይዞሽ አትጨነቂ! ሄደሽ ምግብሽን አዘጋጂ፤ አስቀድመሽ ግን ከዚያችው ካለችሽ ዱቄት ለእኔ ትንሽ እንጐቻ ጋግረሽ አምጪልኝ፤ የቀረውንም ለራስሽና ለልጅሽ ጋግሪው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤልያስም አላት “አትፍሪ፤ ይልቅስ ሄደሽ እንዳልሺው አድርጊ፤ አስቀድመሽ ግን ከዱቄቱ ለእኔ ታናሽ እንጎቻ አድርገሽ አምጭልኝ፤ ከዚያም በኋላ ለአንቺና ለልጅሽ አድርጊ፤ |
በዚያችም ሌሊት እግዚአብሔር ተገለጠለት፤ እንዲህም አለው፥ “እኔ የአባትህ የአብርሃም አምላክ ነኝ፤ አትፍራ፤ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና፤ እባርክሃለሁ፤ ስለ አባትህ ስለ አብርሃም ዘርህን አበዛዋለሁ።”
ሴትየዋም፥ “አምላክህ ሕያው እግዚአብሔርን! በማድጋ ካለው ከእፍኝ ዱቄት በማሰሮም ካለው ከጥቂት ዘይት በቀር እንጀራ የለኝም፤ እነሆም፥ ጥቂት እንጨት እሰበስባለሁ፤ ሄጄም ለእኔና ለልጄ እጋግረዋለሁ፤ በልተነውም እንሞታለን” አለችው።
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በምድር ላይ እግዚአብሔር ዝናብ እስከሚሰጥበት ቀን ድረስ፥ ዱቄቱ ከማድጋው አይጨረስም፥ ዘይቱም ከማሰሮው አይጐድልም።”
እናንተ የምቷጉ አይደላችሁም፤ ይሁዳና ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ተሰለፉ፤ ዝም ብላችሁ ቁሙ፤ የሚሆነውንም የእግዚአብሔርን ማዳን እዩ፤ እግዚአብሔርም ከእናንተ ጋር ነውና አትፍሩ፤ አትደንግጡም፤ ነገም ውጡባቸው።”
ሙሴም ለሕዝቡ፥ “አትፍሩ፤ ዛሬ የምታዩአቸውን ግብፃውያንን ለዘለዓለም አታዩአቸውምና ቁሙ፤ ዛሬ ለእናንተ የሚያደርጋትን የእግዚአብሔርን ማዳን እዩ።
እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፤ እረዳህማለሁ፤ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።
በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ፣ የሰማይንም መስኮት ባልከፍትላችሁ፥ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔ ይልቅም ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም።
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ ‘ጳውሎስ ሆይ፥ አትፍራ፤ በቄሣር ፊት ልትቆም ይገባሃል፤ ከአንተም ጋር የሚሄዱትን ሁሉ እነሆ፥ እግዚአብሔር ለአንተ ሰጥቶሃል።’