La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ነገሥት 13:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ንጉ​ሡም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሰው፥ “ከእኔ ጋር ወደ ቤቴ ና፥ ምሳም ብላ፥ ስጦ​ታም እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ” አለው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ንጉሡም የእግዚአብሔርን ሰው፣ “ዐብረኸኝ ወደ ቤት እንሂድ፤ አንድ ነገር ቅመስ፤ ስጦታም አደርግልሃለሁ” አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከዚህም በኋላ ንጉሡ ነቢዩን “ና ከእኔ ጋር አብረህ ወደ ቤቴ ግባ፤ እህልም ቅመስ፤ ስጦታ እሰጥሃለሁ” አለው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህም በኋላ ንጉሡ ነቢዩን “ና ከእኔ ጋር አብረህ ወደ ቤቴ ግባ፤ እህልም ቅመስ፤ ስጦታ እሰጥሃለሁ” አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ንጉሡም የእግዚአብሔርን ሰው “ከእኔ ጋር ወደ ቤቴ ና፤ እንጀራም ብላ፤ በረከትም እሰጥሃለሁ፤” አለው።

Ver Capítulo



1 ነገሥት 13:7
10 Referencias Cruzadas  

ከዛ​ፉም ሥር ዕረፉ፤ እን​ጀ​ራም እና​ም​ጣ​ላ​ች​ሁና ብሉ፤ ከዚ​ያም በባ​ሪ​ያ​ችሁ ዘንድ ከአ​ረ​ፋ​ችሁ በኋላ፥ ወደ ዐሰ​ባ​ች​ሁት ትሄ​ዳ​ላ​ችሁ።” እነ​ር​ሱም፥ “እን​ዳ​ልህ እን​ዲሁ አድ​ርግ” አሉት።


በእ​ጅ​ሽም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ዐሥር እን​ጀ​ራና የወ​ይን እሸት አን​ድም ማሠሮ ማር ይዘሽ ወደ እርሱ ሂጂ፤ በል​ጁም የሚ​ሆ​ነ​ውን ይነ​ግ​ር​ሻል” አላት።


እር​ሱም ከጭ​ፍ​ራው ሁሉ ጋር ወደ ኤል​ሳዕ ተመ​ለሰ፤ ወደ እር​ሱም ደርሶ በፊቱ ቆመና፥ “እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነው እንጂ በም​ድር ሁሉ አም​ላክ እን​ደ​ሌለ ዐወ​ቅሁ፤ አሁ​ንም ከአ​ገ​ል​ጋ​ይህ በረ​ከት ተቀ​በል” አለው።


እር​ሱም ገና ሳይ​መ​ለስ፥ “የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በይ​ሁዳ ከተ​ሞች ላይ ወደ ሾመው ወደ ሳፋን ልጅ ወደ አኪ​ቃም ልጅ ወደ ጎዶ​ል​ያስ ተመ​ለስ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር በሕ​ዝቡ መካ​ከል በይ​ሁዳ ምድር ተቀ​መጥ፤ ወይም ትሄድ ዘንድ ለዐ​ይ​ንህ ደስ ወደ​ሚ​ያ​ሰ​ኝህ ስፍራ ሂድ” አለው። የአ​ዛ​ዦ​ችም አለቃ ስን​ቅና ስጦታ ሰጥቶ አሰ​ና​በ​ተው።


በመሠዊያዬ ላይ እሳትን በከንቱ እንዳታቃጥሉ ከእናንተ ዘንድ ደጅ የሚዘጋ ሰው ምነው በተገኘ! በእናንተ ደስ አይለኝም፥ ቍርባንንም ከእጃችሁ አልቀበልም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ ሳይሆን፥ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘት ሳይሆን ጐብኙት፤


ማኑ​ሄም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መል​አክ፥ “የፍ​የል ጠቦት እና​ዘ​ጋ​ጅ​ልህ ዘንድ ግድ እን​ል​ሃ​ለን” አለው።


ወደ ቤቱም አስ​ገ​ባው፤ ለአ​ህ​ዮ​ቹም ገፈራ ጣለ​ላ​ቸው፤ እግ​ራ​ቸ​ው​ንም ታጠቡ፤ በሉም፤ ጠጡም።