Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ነገሥት 13:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ከዚህም በኋላ ንጉሡ ነቢዩን “ና ከእኔ ጋር አብረህ ወደ ቤቴ ግባ፤ እህልም ቅመስ፤ ስጦታ እሰጥሃለሁ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ንጉሡም የእግዚአብሔርን ሰው፣ “ዐብረኸኝ ወደ ቤት እንሂድ፤ አንድ ነገር ቅመስ፤ ስጦታም አደርግልሃለሁ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ከዚህም በኋላ ንጉሡ ነቢዩን “ና ከእኔ ጋር አብረህ ወደ ቤቴ ግባ፤ እህልም ቅመስ፤ ስጦታ እሰጥሃለሁ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ንጉ​ሡም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሰው፥ “ከእኔ ጋር ወደ ቤቴ ና፥ ምሳም ብላ፥ ስጦ​ታም እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ንጉሡም የእግዚአብሔርን ሰው “ከእኔ ጋር ወደ ቤቴ ና፤ እንጀራም ብላ፤ በረከትም እሰጥሃለሁ፤” አለው።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 13:7
10 Referencias Cruzadas  

ከዚህም በኋላ ከተከታዮቹ ጋር ወደ እግዚአብሔር ሰው ተመልሶ መጥቶ፦ “ከእስራኤል አምላክ በቀር ሌላ አምላክ አለመኖሩን እነሆ፥ አሁን ተረዳሁ፤ ስለዚህም ጌታዬ ሆይ፥ እባክህ ይህን ስጦታ ተቀበለኝ” አለው።


በዐደራ የተሰጣችሁን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ መንጋውን የምትጠብቁትም በግድ ሳይሆን እግዚአብሔር በሚፈልገው ዐይነት፥ በፈቃደኛነት ይሁን፤ ለገንዘብ በመስገብገብ ሳይሆን ለማገልገል ባላችሁ ፍላጎት ይሁን።


የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “በመሠዊያዬ ላይ ከንቱ እሳትን ከምታቃጥሉበት ይልቅ የቤተ መቅደሱን በር የሚዘጋ ምነው ከእናንተ አንድ ሰው እንኳ በተገኘ! በእናንተ ደስ ስለማይለኝ ለእኔ የምታቀርቡትን ቊርባን አልቀበልም፤


እኔም መልስ ሳልሰጥ ናቡዛርዳን “እንግዲያውስ የሳፋን የልጅ ልጅ ወደ ሆነው ወደ አሒቃም ልጅ ወደ ገዳልያ ዘንድ ሂድ፤ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ገዳልያን የይሁዳ ከተሞች ገዢ አድርጎ ሾሞታል፤ ስለዚህም ከእርሱ ጋር ሆነህ በሕዝቡ መካከል መኖር ትችላለህ፤ ወይም ይጠቅመኛል ብለህ ወደምታስበው ስፍራ ሁሉ መሄድ ትችላለህ።” ከዚያም በኋላ ልዩ ስጦታና ይዤው የምሄደውንም ስንቅ ሰጥቶ አሰናበተኝ።


ስለዚህ ወደ ቤት ወሰዳቸውና ለአህዮቹ ገፈራ መገበለት፤ እንግዶቹም እግራቸውን ታጥበው ራታቸው በሉም ጠጡ።


ማኑሄም የእግዚአብሔርን መልአክ “አንድ የፍየል ጠቦት ዐርደን እስክናዘጋጅልህ ድረስ እባክህ ቈይልን!” አለው።


ወደ እኔ ወደ አገልጋያችሁ በመምጣታችሁ ደስ ብሎኛል፤ ስለዚህ ለጒዞአችሁ ብርታት የሚሰጣችሁን ጥቂት ምግብ አምጥቼ እንዳስተናግዳችሁ ፍቀዱልኝ።” እነርሱም “መልካም ነው፤ እንዳልከው አድርግ” አሉት።


ዐሥር እንጀራ፥ ጥቂት ሙልሙል ዳቦና አንድ ገንቦ ማር. ውሰጂለት፤ ስለ ልጁ ሁኔታ እርሱ ይነግርሻል።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios