1 ነገሥት 11:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አዴርም በግብፅ ሳለ ዳዊት እንደ አባቶቹ እንዳንቀላፋ፥ የሠራዊቱም አለቃ ኢዮአብ እንደ ሞተ በሰማ ጊዜ አዴር ፈርዖንን፥ “ወደ ሀገሬ እሄድ ዘንድ አሰናብተኝ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሃዳድ በግብጽ ሳለ ዳዊት ከአባቶቹ ጋራ ማንቀላፋቱን፣ የሰራዊቱ አዛዥ ኢዮአብም መሞቱን ሰማ። ሃዳድም ፈርዖንን፣ “ወደ አገሬ እንድመለስ አሰናብተኝ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሀዳድ በግብጽ ሳለ የንጉሥ ዳዊትንና የሠራዊቱን አዛዥ የኢዮአብን መሞት በሰማ ጊዜ “ወደ አገሬ ተመልሼ እንድሄድ አሰናብተኝ” ሲል ንጉሡን ጠየቀ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሀዳድ በግብጽ ሳለ የንጉሥ ዳዊትንና የሠራዊቱን አዛዥ የኢዮአብን መሞት በሰማ ጊዜ “ወደ አገሬ ተመልሼ እንድሄድ አሰናብተኝ” ሲል ንጉሡን ጠየቀ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሃዳድም በግብጽ ሳለ ዳዊት ከአባቶቹ ጋር እንዳንቀላፋ፥ የሠራዊቱም አለቃ ኢዮአብ እንደ ሞተ በሰማ ጊዜ፥ ሃዳድ ፈርዖንን “ወደ አገሬ እሄድ ዘንድ አሰናብተኝ፤” አለው። |
አበኔርም ዳዊትን፥ “ተነሥቼ ልሂድ፤ ካንተ ጋርም ቃል ኪዳን እንዲያደርጉ፥ ነፍስህም እንደ ወደደች ሁሉን እንድትገዛ እስራኤልን ሁሉ ለጌታዬ ለንጉሥ ልሰብስብ” አለው። ዳዊትም አበኔርን አሰናበተው፤ በሰላምም ሄደ።
የቴቄምናስ እኅት ወንድ ልጅ ጌንባትን ለአዴር ወለደችለት፤ ቴቄምናስም በፈርዖን ልጆች መካከል አሳደገችው፤ ጌንባትም በፈርዖን ልጆች መካከል ነበረ።
ፈርዖንም፥ “እነሆ፥ ከእኔ ዘንድ ወደ ሀገርህ መሄድ የፈለግህ ምን አጥተህ ነው?” አለው። አዴርም፥ “አንዳች አላጣሁም፤ ነገር ግን ልሂድ” ብሎ መለሰ። አዴርም ወደ ሀገሩ ተመለሰ።
ከብዙ ዘመንም በኋላ የግብፅ ንጉሥ ሞተ። እግዚአብሔርም ሙሴን በምድያም፥ “ነፍስህን የሚሹአት ሰዎች ሁሉ ሞተዋልና ተመልሰህ ወደ ግብፅ ሂድ” አለው።
እርስዋም፥ “እንደ ቃላችሁ ይሁን” አለች፤ አሰናበተቻቸውም፤ እነርሱም ሄዱ፤ ቀዩንም ፈትል በመስኮቱ በኩል አንጠለጠለችው።
ማልደውም ተነሡ፤ በነጋም ጊዜ ሳሙኤል ሳኦልን፥ “ከሰገነቱ ላይ ጠርቶ፦ ተነሣና ላሰናብትህ” አለው። ሳኦልም ተነሣ፤ እርሱና ሳሙኤልም ሁለቱ ወደ ሜዳ ወጡ።