1 ነገሥት 11:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር የእስራኤልን ልጆች፥ “አምላኮቻቸውን ትከተሉ ዘንድ ልባችሁን እንዳይመልሱ ወደ እነርሱ አትግቡ፥ እነርሱም ወደ እናንተ አይግቡ” ካላቸው ከአሕዝብ አገባ፤ ሰሎሞን ግን እነርሱን ተከተለ፤ ወደዳቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህም እግዚአብሔር እስራኤላውያንን፣ “ልባችሁን ወደ አማልክታቸው በርግጥ ይመልሱታልና ከእነርሱ ጋራ መጋባት የለባችሁም” ካላቸው አሕዛብ ወገን ነበሩ፤ ሆኖም ሰሎሞን ከእነዚሁ ጋራ ፍቅሩ ጠና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ለእስራኤላውያን፥ “አሕዛብ ሴቶችን ያገባችሁ እንደሆነ በእርግጥ ወደ አማልእክታቸው ስለሚስቡአችሁ እነርሱን አታግቡ” ብሎ አስጠንቅቆአቸው ነበር፤ እነዚህን ሰሎሞን የወደዳቸው ሴቶች ጌታ እንዳይጋቡ ከከለከላቸው ሕዝቦች መካከል ናቸው፤ ሰሎሞን ግን ከእነርሱ ጋር በፍቅር ተሰባበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን፥ “አሕዛብ ሴቶችን ያገባችሁ እንደ ሆነ በእርግጥ ወደ አማልእክታቸው ስለሚስቡአችሁ እነርሱን አታግቡ” ብሎ አስጠንቅቆአቸው ነበር፤ እነዚህን ሰሎሞን የወደዳቸው ሴቶች እግዚአብሔር እንዳይጋቡ ከከለከላቸው ሕዝቦች መካከል ናቸው፤ ሰሎሞን ግን ከእነርሱ ጋር በፍቅር ተሰባበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር የእስራኤልን ልጆች “አምላኮቻቸውን ትከተሉ ዘንድ ልባችሁን በእውነት ያዘነብላሉና ወደ እነርሱ አትግቡ፤ እነርሱም ወደ እናንተ አይግቡ፤” ካላቸው ከአሕዛብ፥ ከእነዚህ ጋር ሰሎሞን በፍቅር ተጣበቀ። |
ልቡናውም በያዕቆብ ልጅ በዲና ፍቅር ተነደፈ፤ ብላቴናዪቱንም ወደዳት፤ ልብዋንም ደስ በሚያሰኛት ነገር ተናገራት።
ሁለት ጊዜም ከተገለጠለት ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ልቡናውን መልሶአልና እግዚአብሔር በሰሎሞን ላይ ቍጣን ተቈጣ።
ነቢዩ የአናኒ ልጅ ኢዩ ሊገናኘው ወጣ፤ ንጉሡንም ኢዮሣፍጥን፥ “ኀጢአተኛውን ታግዛለህን? ወይስ እግዚአብሔር የሚጠላውን ትወድዳለህን? ስለዚህም ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ ቍጣ መጥቶብሃል።
የአክዓብንም ልጅ አግብቶ ነበርና የአክዓብ ቤት እንዳደረገ በእስራኤል ነገሥታት መንገድ ሄደ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ አደረገ።
አሁንም ትበረቱ ዘንድ፥ የምድሩንም ፍሬ ትበሉ ዘንድ፥ ልጆቻችሁም ለዘለዓለም ይወርሱአት ዘንድ፥ ሴቶችን ልጆቻችሁን ለወንዶች ልጆቻቸው አትስጡ፤ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለወንዶች ልጆቻችሁ አትውሰዱ፤ ሰላማቸውንና ደኅንነታቸውንም ለዘለዓለም አትሹ።
ድንበርህንም ከኤርትራ ባሕር እስከ ፍልስጥኤም ባሕር፥ ከምድረ በዳም እስከ ታላቁ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ አሰፋለሁ፤ በምድር የሚኖሩትን በእጅህ እጥላለሁና፤ ከአንተም አስወጣቸዋለሁ።
በመካከልህ ወጥመድ እንዳይሆኑብህ አንተ በምትገባበት ምድር ከሚኖሩ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን እንዳታደርግ ተጠንቀቅ፤
ሴቶች ልጆቻቸውምንም ከወንድ ልጆችህ፥ ሴቶች ልጆችህንም ከወንድ ልጆቻቸው ጋር እንዳታጋባ፥ ልጆቻቸውም አምላኮቻቸውን ተከትለው ሲያመነዝሩ ከአምላኮቻቸው በኋላ ሄደው አመንዝረውም ልጆችህን እንዳያስቱ ተጠንቀቅ።
እግዚአብሔር የወደደውን መቅደስ ይሁዳ አርክሶአልና፥ የእንግዳውንም አምላክ ልጅ ሚስት አድርጎ አግብቶአልና ይሁዳ አታልሎአል፥ በእስራኤልና በኢየሩሳሌም ውስጥ ርኵሰት ተሠርቶአል።
ይህን እንዲህ ላደረገ ሞት እንደሚገባው እነርሱ ራሳቸው የእግዚአብሔርን ፍርድ እያወቁ፥ እነርሱ ብቻ የሚያደርጉት አይደለም፤ ነገር ግን ሌላውን ያነሣሡታል፤ ያሠሩታልም።