1 ነገሥት 10:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በግመሎችም ላይ ሽቱና እጅግ ብዙ ወርቅ የከበረም ዕንቍ አስጭና ከታላቅ ጓዝ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ገባች፤ ወደ ሰሎሞንም በመጣች ጊዜ በልብዋ ያለውን ሁሉ ነገረችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታላቅ አጀብ አስከትላ ሽቱ፣ እጅግ ብዙ ወርቅና የከበሩ ድንጋዮችን በግመሎች አስጭና ኢየሩሳሌም ከደረሰች በኋላ፣ ወደ ሰሎሞን ገብታ በልቧ ያለውን ጥያቄ ሁሉ አቀረበችለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብዙ የክብር አጃቢዎችን በማስከተል በግመሎች የተጫኑ ሽቶ፥ የከበረ ዕንቁና ብዙ ወርቅ ይዛ መጣች፤ ከሰሎሞንም ጋር በተገናኙ ጊዜ በሐሳብዋ ያለውን ጥያቄ ሁሉ አቀረበችለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብዙ የክብር አጃቢዎችን በማስከተል በግመሎች የተጫነ ሽቶ፥ የከበረ ዕንቊና ብዙ ወርቅ ይዛ መጣች፤ ከሰሎሞንም ጋር በተገናኙ ጊዜ በሐሳብዋ ያለውን ጥያቄ ሁሉ አቀረበችለት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በግመሎችም ላይ ሽቱና እጅግ ብዙ ወርቅ የከበረም ዕንቁ አስጭና ከታላቅ ጓዝ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ገባች፤ ወደ ሰሎሞንም በመጣች ጊዜ በልብዋ ያለውን ሁሉ አጫወተችው። |
ለንጉሡም መቶ ሃያ መክሊት ወርቅ እጅግም ብዙ ሽቶ፥ የከበረም ዕንቍ ሰጠችው፤ የሳባ ንግሥት ለንጉሡ ለሰሎሞን እንደ ሰጠችው ያለ የሽቶ ብዛት ከዚያ ወዲያ አልመጣም ነበር።
ሕዝቅያስም በእነርሱ ደስ አለው፤ ግምጃ ቤቱንም ሁሉ፥ ብሩንና ወርቁንም፥ ሽቱውንና የከበረውንም ዘይት፥ መሣሪያም ያለበትን ቤት በቤተ መዛግብቱም የተገኘውን ሁሉ አሳያቸው፤ በቤቱና በግዛቱ ሁሉ ካለው ሕዝቅያስ ያላሳያቸው የለም።
የሶርያም ንጉሥ ንዕማንን፥ “ሂድ፥ ለእስራኤል ንጉሥ ደብዳቤ እልካለሁ” አለው። እርሱም ሄደ፤ ዐሥርም መክሊት ብር፥ ስድስት ሺህም ወቄት ወርቅ፥ ዐሥርም መለወጫ ልብስ በእጁ ወሰደ።
ተባትና እንስት አንበሳ፥ እፉኝትም፥ ነዘር እባብም፥ በሚወጡባት በመከራና በጭንቀት ምድር በኩል ብልጽግናቸውን በአህዮች ጫንቃ ላይ፥ መዛግብቶቻቸውንም በግመሎች ሻኛ ላይ እየጫኑ ወደማይጠቅሙአቸው ሕዝብ ይሄዳሉ።
የሳባና የራዕማ ነጋዴዎች እነዚህ ነጋዴዎችሽ ነበሩ፤ ንግድሽን በጥሩ ሽቱና በከበረ ድንጋይ ሁሉ፥ በወርቅም አደረጉ።
በማግሥቱም አግሪጳና በርኒቄ በብዙ ግርማ መጡ፤ ከመሳፍንቱና ከከተማው ታላላቅ ሰዎች ጋርም ወደ ፍርድ ቤት ገቡ፤ ፊስጦስም ጳውሎስን እንዲያመጡት አዘዘ።