La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ነገሥት 1:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ነገር ግን ካህኑ ሳዶ​ቅና የዮ​ዳሄ ልጅ በና​ያስ ነቢ​ዩም ናታን፥ ሳሚም፥ ሬሲም፥ የዳ​ዊ​ትም ኀያ​ላን አዶ​ን​ያ​ስን አል​ተ​ከ​ተ​ሉም ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ነገር ግን ካህኑ ሳዶቅ፣ የዮዳሄ ልጅ በናያስ፣ ነቢዩ ናታን፣ ሳሚ፣ ሬሲና የዳዊት የክብር ዘበኞች ከአዶንያስ ጋራ አልተባበሩም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ነገር ግን ካህኑ ሳዶቅና የዮዳሄ ልጅ በናያ፥ ነቢዩም ናታን፥ ሺምዒና ሬዒ፥ የዳዊትም ተዋጊዎች ከአዶንያስ ጋር አልነበሩም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ነገር ግን ካህኑ ሳዶቅ፥ የዮዳሄ ልጅ በናያ፥ ነቢዩ ናታን፥ ሺምዒ፥ ሬዒና የዳዊት የክብር ዘበኞች አዶንያስን አልደገፉም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ነገር ግን ካህኑ ሳዶቅና የዮዳሄ ልጅ በናያስ ነቢዩም ናታን ሳሚም ሬሲም የዳዊትም ኀያላን ከአዶንያስ ጋር አልነበሩም።

Ver Capítulo



1 ነገሥት 1:8
17 Referencias Cruzadas  

ደግ​ሞም በነ​ቢዩ በና​ታን እጅ ልኮ ስሙን ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍቁረ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብሎ ጠራው።


ኢዮ​አ​ብም በእ​ስ​ራ​ኤል ሠራ​ዊት ሁሉ ላይ አለቃ ነበረ፤ የዮ​ዳ​ሄም ልጅ በና​ያስ በከ​ሊ​ታ​ው​ያ​ንና በፈ​ሊ​ታ​ው​ያን ላይ አለቃ ነበረ፤


ሱሳም ጸሓፊ ነበረ፤ ሳዶ​ቅና አብ​ያ​ታ​ርም ካህ​ናት ነበሩ፤


ነገር ግን እኔን አገ​ል​ጋ​ይ​ህን፥ ካህ​ኑ​ንም ሳዶ​ቅን፥ የዮ​ዳ​ሄ​ንም ልጅ በና​ያ​ስን፥ አገ​ል​ጋ​ይ​ህ​ንም ሰሎ​ሞ​ንን አል​ጠ​ራም።


ንጉ​ሡም ዳዊት፥ “ካህ​ኑን ሳዶ​ቅ​ንና ነቢዩ ናታ​ንን የዮ​ዳ​ሄ​ንም ልጅ በና​ያ​ስን ጥሩ​ልኝ” አለ።


ካህ​ኑም ሳዶ​ቅና ነቢዩ ናታን የዮ​ዳ​ሄም ልጅ በና​ያስ ከሊ​ታ​ው​ያ​ንና ፈሊ​ታ​ው​ያ​ንም ወረዱ፤ ሰሎ​ሞ​ን​ንም በን​ጉሡ በዳ​ዊት በቅሎ ላይ አስ​ቀ​ም​ጠው ወደ ግዮን ወሰ​ዱት።


ንጉ​ሡም በእ​ርሱ ፋንታ የዮ​ዳ​ሄን ልጅ በን​ያ​ስን የሠ​ራ​ዊቱ አለቃ አድ​ርጎ ሾመ፤ መን​ግ​ሥ​ቱም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ጸናች። በአ​ብ​ያ​ታ​ርም ፋንታ ካህ​ኑን ሳዶ​ቅን ሾመ።


በብ​ን​ያም የኤላ ልጅ ሳሚ ነበረ፤


ካህ​ኑን ሳዶ​ቅ​ንና ካህ​ና​ቱን ወን​ድ​ሞ​ቹን በገ​ባ​ዖን በኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገጃ ባለው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማደ​ሪያ ፊት አቆ​ማ​ቸው፥


“ነገር ግን የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከእኔ ዘንድ በሳቱ ጊዜ የመ​ቅ​ደ​ሴን ሥር​ዐት የጠ​በቁ የሳ​ዶቅ ልጆች ሌዋ​ው​ያን ካህ​ናት ያገ​ለ​ግ​ሉኝ ዘንድ ወደ እኔ ይቀ​ር​ባሉ፤ ስቡ​ንና ደሙ​ንም ወደ እኔ ያቀ​ርቡ ዘንድ በፊቴ ይቆ​ማሉ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


የሌዊ ቤት ወገን ለብቻው፥ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፣ የሰሜኢ ወገን ለብቻው፥ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፣