Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ነገሥት 2:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 ንጉ​ሡም በእ​ርሱ ፋንታ የዮ​ዳ​ሄን ልጅ በን​ያ​ስን የሠ​ራ​ዊቱ አለቃ አድ​ርጎ ሾመ፤ መን​ግ​ሥ​ቱም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ጸናች። በአ​ብ​ያ​ታ​ርም ፋንታ ካህ​ኑን ሳዶ​ቅን ሾመ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 ንጉሡም በኢዮአብ ቦታ የዮዳሄን ልጅ በናያስን በሰራዊቱ ላይ ሾመ፤ በአብያታርም ቦታ ካህኑን ሳዶቅን ተካ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 ንጉሥ ሰሎሞን በኢዮአብ ፈንታ በናያን የሠራዊቱ አዛዥ፥ በአብያታርም ፈንታ ሳዶቅን ካህን አድርጎ ሾመ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 ንጉሥ ሰሎሞን በኢዮአብ ፈንታ በናያን የሠራዊቱ አዛዥ፥ በአብያታርም ፈንታ ሳዶቅን ካህን አድርጎ ሾመ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 ንጉሡም በእርሱ ፋንታ የዮዳሄን ልጅ በናያስን የሠራዊቱ አለቃ አደረገ፤ በአብያታርም ፋንታ ካህኑን ሳዶቅን አደረገ።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 2:35
19 Referencias Cruzadas  

በሴ​ሎም በዔሊ ቤት ላይ የተ​ና​ገ​ረው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ይፈ​ጸም ዘንድ ሰሎ​ሞን አብ​ያ​ታ​ርን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክህ​ነት አወ​ጣው።


በዚ​ያም ቀን በታ​ላቅ ደስታ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በሉ፥ ጠጡም። የዳ​ዊ​ት​ንም ልጅ ሰሎ​ሞ​ንን ሁለ​ተኛ ጊዜ አነ​ገ​ሡት፤ እር​ሱ​ንም ንጉሥ ይሆን ዘንድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀቡት፤ ሳዶ​ቅም በካ​ህ​ናት ላይ ተሾመ።


ዳዊ​ትም ከአ​ል​ዓ​ዛር ልጆች ሳዶ​ቅን፥ ከኢ​ታ​ም​ርም ልጆች አቤ​ሜ​ሌ​ክን እንደ ቍጥ​ራ​ቸው፥ እንደ አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸ​ውና እንደ እየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች ከፍሎ መደ​ባ​ቸው።


የዮ​ዳ​ሄም ልጅ በን​ያስ የሠ​ራ​ዊት አለቃ ነበረ፤ ሳዶ​ቅና አብ​ያ​ታ​ርም ካህ​ናት ነበሩ፤


በመ​ዝ​ሙር መጽ​ሐፍ ‘መኖ​ሪ​ያዉ ምድረ በዳ ትሁን፤ በው​ስ​ጧም የሚ​ኖር አይ​ኑር፤ ሹመ​ቱ​ንም ሌላ ይው​ሰድ’ ተብሎ ተጽ​ፎ​አ​ልና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ታች ወደ ሰዎች ይመ​ለ​ከ​ታል፥ ሊመ​ረ​መሩ የማ​ይ​ችሉ ነገ​ሮ​ችን ሁሉ፥ ቍጥር የሌ​ላ​ቸ​ውን የተ​ከ​በ​ሩ​ት​ንና ድን​ቆ​ች​ንም ያስ​ተ​ው​ላል።


የታ​መነ ካህን ለእኔ አስ​ነ​ሣ​ለሁ፤ በል​ቤም፥ በነ​ፍ​ሴም እን​ዳለ እን​ዲሁ ያደ​ር​ጋል፤ እኔም የታ​መነ ቤት እሠ​ራ​ለ​ታ​ለሁ፤ ዘመ​ኑን ሁሉ እኔ በቀ​ባ​ሁት ሰው ፊት ይሄ​ዳል።


ዳዊ​ትም ካህ​ና​ቱን ሳዶ​ቅ​ንና አብ​ያ​ታ​ርን፥ ሌዋ​ው​ያ​ን​ንም፥ ኡር​ኤ​ልን፥ ዓሣ​ያን፥ ኢዮ​ኤ​ልን፥ ሰማ​ያን፥ ኤሊ​ኤ​ልን፥ አሚ​ና​ዳ​ብ​ንም ጠርቶ፦


ወደ ሰሜ​ንም የሚ​መ​ለ​ከ​ተው ቤት መሠ​ዊ​ያ​ዉን ለማ​ገ​ል​ገል ለሚ​ተጉ ካህ​ናት ነው፤ እነ​ዚህ ከሌዊ ልጆች መካ​ከል ያገ​ለ​ግ​ሉት ዘንድ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቀ​ርቡ የሳ​ዶቅ ልጆች ናቸው” አለኝ።


ያገ​ለ​ግ​ሉኝ ዘንድ ወደ እኔ ለሚ​ቀ​ርቡ ከሳ​ዶቅ ዘር ለሚ​ሆኑ ለሌ​ዋ​ው​ያኑ ካህ​ናት ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ውን ከመ​ን​ጋው አንድ ወይ​ፈን ትሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ነገር ግን እኔን አገ​ል​ጋ​ይ​ህን፥ ካህ​ኑ​ንም ሳዶ​ቅን፥ የዮ​ዳ​ሄ​ንም ልጅ በና​ያ​ስን፥ አገ​ል​ጋ​ይ​ህ​ንም ሰሎ​ሞ​ንን አል​ጠ​ራም።


ወደ ንጉ​ሡም ገቡ። ንጉ​ሡም አላ​ቸው፥ “የጌ​ታ​ች​ሁን አገ​ል​ጋ​ዮች ይዛ​ችሁ ሂዱ፥ ልጄ​ንም ሰሎ​ሞ​ንን በበ​ቅ​ሎዬ ላይ አስ​ቀ​ም​ጡት፥ ወደ ግዮ​ንም አው​ር​ዱት፤


ካህ​ኑም ሳዶ​ቅና ነቢዩ ናታን የዮ​ዳ​ሄም ልጅ በና​ያስ ከሊ​ታ​ው​ያ​ንና ፈሊ​ታ​ው​ያ​ንም ወረዱ፤ ሰሎ​ሞ​ን​ንም በን​ጉሡ በዳ​ዊት በቅሎ ላይ አስ​ቀ​ም​ጠው ወደ ግዮን ወሰ​ዱት።


በሦ​ስ​ተ​ኛው ወር ሦስ​ተ​ኛው የጭ​ፍራ አለቃ የካ​ህኑ የዮ​ዳሄ ልጅ በና​ያስ ነበረ፤ በእ​ር​ሱም ክፍል ሃያ አራት ሽህ ጭፍራ ነበረ።


የሰ​ሎም ልጅ፥ የሳ​ዶቅ ልጅ፥ የአ​ኪ​ጦብ ልጅ፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios