ናታንም የሰሎሞንን እናት ቤርሳቤህን እንዲህ ብሎ ተናገራት፥ “ጌታችን ዳዊት ሳያውቅ የአጊት ልጅ አዶንያስ እንደ ነገሠ አልሰማሽምን?
1 ነገሥት 1:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሄደሽ ወደ ንጉሡ ወደ ዳዊት ግቢና፦ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ለእኔ ለአገልጋይህ፦ ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ይነግሣል፤ በዙፋኔም ይቀመጣል ብለህ አልማልህልኝምን? ስለምንስ አዶንያስ ይነግሣል? በዪው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ንጉሥ ዳዊት ሂጂና፣ ‘ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፤ “ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ ቀጥሎ ይነግሣል፤ በዙፋኔም ይቀመጣል” ብለህ ለእኔ ለአገልጋይህ አልማልህልኝም ነበር? ታዲያ አዶንያስ የነገሠው ስለ ምንድን ነው?’ በዪው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሄደሽ ወደ ንጉሡ ወደ ዳዊት ግቢና፦ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ለእኔ ለባርያህ፦ ‘ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ይነግሣል፥ በዙፋኔም ይቀመጣል’ ብለህ አልማልህልኝምን? ስለ ምንስ አዶንያስ ይነግሣል? በዪው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ንጉሥ ዳዊት ገብተሽ ‘ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ነግሦ በዙፋኔ ይቀመጣል’ ብለህ ለአገልጋይህ በመሐላ ቃል ገብተህልኝ አልነበረምን? ታዲያ፥ አሁን አዶንያስ እንዴት ሊነግሥ ቻለ? ብለሽ ንገሪው”። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሄደሽ ወደ ንጉሡ ወደ ዳዊት ግቢና ‘ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! ለእኔ ለባሪያህ ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ይነግሣል፤ በዙፋኔም ይቀመጣል፤ ብለህ አልማልህልኝምን? ስለ ምንስ አዶንያስ ይነግሣል?’ በዪው። |
ናታንም የሰሎሞንን እናት ቤርሳቤህን እንዲህ ብሎ ተናገራት፥ “ጌታችን ዳዊት ሳያውቅ የአጊት ልጅ አዶንያስ እንደ ነገሠ አልሰማሽምን?
እርስዋም አለችው፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ አንተ ለአገልጋይህ፦ ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ይነግሣል፤ በዙፋኔም ይቀመጣል ብለህ በአምላክህ ምለህልኝ አልነበረምን?
በእውነት፦ ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ይነግሣል፤ በእኔም ፋንታ በዙፋኔ ላይ ይቀመጣል ብዬ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር እንደ ማልሁልሽ፥ እንዲሁ ዛሬ በእውነት አደርጋለሁ።”
በኋላውም ተከትላችሁ ውጡ፤ እርሱም መጥቶ በዙፋኔ ላይ ይቀመጥ፤ በእኔም ፋንታ ይንገሥ፤ በእስራኤልና በይሁዳም ላይ ይነግሥ ዘንድ አዝዣለሁ።”
ንጉሡም፥ “ዐይኔ እያየ ዛሬ በዙፋኔ ላይ የሚቀመጠውን ዘር የሰጠኝ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን” አለ።
እግዚአብሔርም ብዙ ልጆች ሰጥቶኛልና ከልጆቼ ሁሉ በእግዚአብሔር መንግሥት ዙፋን ላይ ተቀምጦ በእስራኤል ላይ ይነግሥ ዘንድ ልጄን ሰሎሞንን መርጦታል።
ለአለቆች ሰላምን ለእርሱም ሕይወትን አመጣለሁና፤ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም ድረስ በፍርድና በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ ግዛቱ ታላቅ ይሆናል፤ በዳዊት ዙፋን መንግሥቱ ትጸናለች፤ ለሰላሙም ፍጻሜ የለውም። የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቅንዐት ይህን ያደርጋል።
በዙፋኑ ላይ የሚነግሥ ልጅ እንዳይሆንለት ከባሪያዬ ከዳዊት ጋር፥ ከአገልጋዮችም ከሌዋውያን ካህናት ጋር ያለው ቃል ኪዳኔ ደግሞ ይፈርሳል።