በውኑ ልንበላና ልንጠጣ አይገባንምን?
ለመሆኑ፣ የመብላትና የመጠጣት መብት የለንምን?
ልንበላና ልንጠጣ መብት የለንምን?
እኛ ምግብና መጠጥ የማግኘት መብት የለንምን?
ፀሐይም በገባች ጊዜ ንጹሕ ይሆናል፤ ከዚያም በኋላ ምግቡ ነውና ከተቀደሰው ይብላ።
ወይም ለመንገድ ከረጢት ወይም ሁለት እጀ ጠባብ ወይም ጫማ ወይም በትር አትያዙ፤ ለሠራተኛ ምግቡ ይገባዋልና።
በዚያም ቤት ተቀመጡ፤ ከእነርሱ የተገኘውንም ብሉ፥ ጠጡም፤ ለሠራተኛ ዋጋው ይገባዋልና፤ ከቤትም ወደ ቤት አትሂዱ።
ወርቅም ቢሆን፥ ብርም ቢሆን፥ ልብስም ቢሆን ከእናንተ ከአንዱ ስንኳ አልተመኘሁም።
ለሚከራከሩኝ መልሴ እንዲህ ነው።
ይህንም ነገር ንኡሰ ክርስቲያን ይስማው፤ መልካሙንም ነገር ሁሉ ከሚያስተምረው ይማር።
የክርስቶስም ሐዋርያት እንደ መሆናችን ልንከብድባችሁ ስንችል፥ ከእናንተ ቢሆን ወይም ከሌሎች ክብርን ከሰው አልፈለግንም።
ወንድሞች ሆይ! ድካማችንና ጥረታችን ትዝ ይላችኋል፤ ከእናንተ በአንዱ ስንኳ እንዳንከብድበት ሌሊትና ቀን እየሠራን፥ የእግዚአብሔርን ወንጌል ለእናንተ ሰበክን።