1 ቆሮንቶስ 6:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሌቦች፥ ወይም ቀማኞች፥ ወይም ሰካሮች፥ ወይም ተሳዳቢዎች፥ ወይም ነጣቂዎች፥ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱአትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወይም ሌቦች፣ ስግብግቦች፣ ሰካራሞች፣ ተሳዳቢዎችና ቀማኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወይም ሌቦች ወይም ስግብግቦች ወይም ሰካራሞች ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ነጣቂዎች የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወይም ሌቦች፥ ወይም ስግብግቦች፥ ወይም ሰካራሞች፥ ወይም የሰው ስም አጥፊዎች፥ ወይም ቀማኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወይም ሌቦች ወይም ገንዘብን የሚመኙ ወይም ሰካሮች ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ነጣቂዎች የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም። |
አለቆችሽ ዐመፀኞችና የሌቦች ባልንጀሮች ሆኑ፤ ሁሉ ጉቦ ይወድዳሉ፤ ፍርድንም ሊያጣምሙ ይፈልጋሉ፤ ለሙት ልጅ አይፈርዱም፤ የመበለቲቱንም አቤቱታ አያዳምጡም።
በውስጥዋ ያሉ አለቆችዋ የስስትን ትርፍ ለማግኘት ሲሉ ደምን ያፈስሱ ዘንድ፥ ነፍሶችንም ያጠፉ ዘንድ እንደሚናጠቁ ተኵላዎች ናቸው።
በመንገድም አጠገብ በለስ አይቶ ወደ እርስዋ መጣ፤ ከቅጠልም ብቻ በቀር ምንም አላገኘባትምና “ለዘላለሙ ፍሬ አይገኝብሽ፤” አላት። በለሲቱም ያንጊዜውን ደረቀች።
“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ ወዮላችሁ፤ እናንተ አትገቡም፤ የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።
ይህንም ያለ፥ ድሆች አሳዝነውት አይደለም፤ ሌባ ነበርና፥ ሙዳየ ምጽዋቱንም ሲጠብቅ በውስጡ ከሚገባው ይወስድ ነበርና ስለዚህ ነው እንጂ።
አሁንም ለእግዚአብሔርና ሊያንጻችሁ፥ በቅዱሳንም ሁሉ መካከል ርስትን ሊሰጣችሁ ለሚችለው ለጸጋው ቃል አደራ ሰጥቻችኋለሁ።
ወንድሞቻችን ሆይ፥ ይህን እንነግራችኋለን፦ ሥጋዊና ደማዊ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርስም፥ የሚፈርሰው የማይፈርሰውን አይወርስም።
አሁንም ከወንድሞች መካከል ዘማዊ፥ ወይም ገንዘብን የሚመኝ፥ ወይም ጣዖትን የሚያመልክ፥ ወይም ዐመፀኛ፥ ወይም ተራጋሚ፥ ወይም ሰካራም፥ ወይም የሚቀማ ቢኖር እንደዚህ ካለ ሰው ጋር አንድ እንዳትሆኑ ጻፍሁላችሁ፥ እንደዚህ ካለው ሰው ጋር መብልም እንኳ አትብሉ፤
ሴሰኛ፥ ወይም ኀጢአተኛ፥ ወይም ቀማኛ፥ ወይም ጣዖትን የሚያመልክ ሁሉ በእግዚአብሔር ልጅ በክርስቶስ መንግሥት ዕድል ፋንታ እንደሌለው ይህን ዕወቁ።
አስቀድመን ደግሞ እንዳልናችሁና እንደ መሰከርንላችሁ፥ ጌታ ስለዚህ ነገር ሁሉ የሚበቀል ነውና፥ ማንም በዚህ ነገር አይተላለፍ፤ ወንድሙንም አያታልል።