1 ቆሮንቶስ 2:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቃሌም፥ ትምህርቴም መንፈስንና ኀይልን በመግለጥ ነበር እንጂ በሚያባብል በጥበብ ቃል አልነበረም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቃሌም ስብከቴም የመንፈስን ኀይል በመግለጥ እንጂ፣ በሚያባብል የጥበብ ቃል አልነበረም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቃሌም ስብከቴም መንፈስንና ኃይልን በመግለጥ ነበረ እንጂ፥ በሚያባብል የጥበብ ቃል አልነበረም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንግግሬና ስብከቴ በሰብአዊ ጥበብና ንግግር በማሳመር ሳይሆን በእግዚአብሔር መንፈስ ኀይል የተደገፈ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እምነታችሁም በእግዚአብሔር ኃይል እንጂ በሰው ጥበብ እንዳይሆን፥ ቃሌም ስብከቴም መንፈስንና ኃይልን በመግለጥ ነበረ እንጂ፥ በሚያባብል በጥበብ ቃል አልነበረም። |
በእኔ ላይ የተሰበሰቡና የከበቡኝን የብዙ ሰዎችን ስድብ ሰምቻለሁ፤ መውደቄን የሚጠብቁ የሰላሜ ሰዎች ሁሉ፥ “ምናልባት ይታለል እንደ ሆነ፥ እናሸንፈውም እንደ ሆነ፥ እርሱንም እንበቀል እንደ ሆነ፥ ተነሡ እኛም እንነሣለን” ይላሉ።
እግዚአብሔር ሳይልካቸው፦ እግዚአብሔር ይላል የሚሉ ሰዎች ሐሰትን ያያሉ፤ ከንቱን ያምዋርታሉ፤ ቃሉንም ማጽናት ይጀምራሉ።
የተስፋ አምላክ እግዚአብሔርም በመንፈስ ቅዱስ ኀይል በተስፋ ያበዛችሁ ዘንድ በእምነት ደስታንና ሰላምን ሁሉ ይፈጽምላችሁ።
በኀይልና በተአምራት፥ በመንፈስ ቅዱስ ኀይልና ድንቅ ሥራን በመሥራትም፥ ከኢየሩሳሌም አውራጃዎች ጀምሬ እስከ እልዋሪቆን ድረስ እንደ አስተማርሁ፥ የክርስቶስንም ወንጌል ፈጽሞ እንደ ሰበክሁ እናገር ዘንድ እደፍራለሁ።
እነርሱ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ያይደለ ለሆዳቸው ይገዛሉና፤ በነገር ማታለልና በማለዛዘብም የብዙዎች የዋሃንን ልብ ያስታሉ፤
ክርስቶስ ወንጌልን ለመስበክ እንጂ ለማጥመቅ አልላከኝምና፥ የክርስቶስን መስቀሉን ከንቱ እንዳናደርግ ነገርን በማራቀቅ አይደለም።
ወንድሞቻችን ሆይ፥ እኔም ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ በማባበልና ነገርን በማራቀቅ የእግዚአብሔርን ትምህርት ላስተምራችሁ የመጣሁ አይደለም።
ይህም ትምህርታችን ከሰው የተገኘ ትምህርት አይደለም፤ የአነጋገር ጥበብም አይደለም፤ መንፈስ ቅዱስ የገለጸው ትምህርት ነው እንጂ፤ መንፈሳዊ ጥበብም ከመንፈስ ቅዱስ የሚሆነውን መርምረው ለሚያውቁ ለመንፈሳውያን ነው።
አሁንስ ለእግዚአብሔር ያይደለ ለሰው ብዬ አስተምራለሁን? ወይስ ሰውን ደስ አሰኛለሁን? ሰውን ደስ ላሰኝ ብወድስ የክርስቶስ ባሪያ አይደለሁም።
ወንጌላችን በኀይልና በመንፈስ ቅዱስ በብዙ መረዳትም እንጂ በቃል ብቻ ወደ እናንተ አልመጣምና፤ በእናንተ ዘንድ ስለ እናንተ እንዴት እንደ ነበርን ታውቃላችሁ።
ለእነርሱም ከሰማይ በተላከ በመንፈስ ቅዱስ ወንጌልን የሰበኩላችሁ ሰዎች አሁን ባወሩላችሁ ነገር እናንተን እንጂ ራሳቸውን እንዳላገለገሉ ተገለጠላቸው፤ ይህንም ነገር መላእክቱ ሊመለከቱ ይመኛሉ።
ከዚህ በኋላ በአራተኛው ቀን የሶምሶንን ሚስት፥ “እንቆቅልሹን እንዲነግርሽ ባልሽን አባብይው፤ አለዚያም አንቺንና የአባትሽን ቤት በእሳት እናቃጥላለን፤ ወይስ ወደዚህ የጠራችሁን ልታደኸዩን ነውን?” አሉአት።
የፍልስጥኤማውያን መሳፍንትም ወደ እርስዋ ወጥተው፥ “እርሱን አባብለሽ በእርሱ ያለ ታላቅ ኀይል በምን እንደ ሆነ፥ እኛም እርሱን ለማዋረድ እናስረው ዘንድ የምናሸንፈው በምን እንደ ሆነ ዕወቂ፤ እኛም እያንዳንዳችን ሺህ አንድ መቶ ብር እንሰጥሻለን” አሉአት።