Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መሳፍንት 14:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ከዚህ በኋላ በአ​ራ​ተ​ኛው ቀን የሶ​ም​ሶ​ንን ሚስት፥ “እን​ቆ​ቅ​ል​ሹን እን​ዲ​ነ​ግ​ርሽ ባል​ሽን አባ​ብ​ይው፤ አለ​ዚ​ያም አን​ቺ​ንና የአ​ባ​ት​ሽን ቤት በእ​ሳት እና​ቃ​ጥ​ላ​ለን፤ ወይስ ወደ​ዚህ የጠ​ራ​ች​ሁን ልታ​ደ​ኸ​ዩን ነውን?” አሉ​አት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 በአራተኛው ቀን የሳምሶንን ሚስት፣ “የዕንቈቅልሹን ፍች እንዲነግረን ባልሽን እስኪ አግባቢልን፤ አለዚያ አንቺንም የአባትሽንም ቤተ ሰብ በእሳት እናቃጥላችኋለን፤ ጠርታችሁ የጋበዛችሁን ልትዘርፉን ነው?” አሏት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 በአራተኛው ቀን የሳምሶንን ሚስት፥ “የእንቈቅልሹን ፍች እንዲነግረን ባልሽን እስቲ አግባቢልን፤ ያለዚያ አንቺንም የአባትሽንም ቤተሰብ በእሳት እናቃጥላችኋለን፤ ጠርታችሁ የጋበዛችሁን ልትዘርፉን ነው እንዴ?” አሏት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 በአራተኛው ቀን የሶምሶንን ሚስት እንዲህ አሉአት፤ “ባልሽን አግባብተሽ የእንቆቅልሹን ፍች እንዲነግረን አድርጊ፤ ይህን ካላደረግሽ ግን የአባትሽን ቤት በእሳት አያይዘን አንቺንም በውስጡ በመጨመር እናቃጥልሻለን፤ ለካስ እናንተ ሁለታችሁም ወደ ግብዣችሁ የጠራችሁን ልትዘርፉን ኖሮአልን?”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 በአራተኛውም ቀን የሶምሶንን ሚስት፦ እንቈቅልሹን እንዲነግረን ባልሽን ሸንግዪው፥ አለዚያም አንቺንና የአባትሽን ቤት በእሳት እናቃጥላለን፥ ወደዚህ ጠራችሁን ልትገፉን ነውን? አሉአት።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 14:15
9 Referencias Cruzadas  

“ና ከእኛ ጋር ደምን በማፍሰስ አንድ ሁን፥ ጻድቅ ሰውንም በምድር እንቅበር፥ ብለው ቢማልዱህ፥


ከአመንዝራ ሴት ከንፈር ማር ይንጠባጠባልና፥ ወደ አመንዝራ ሴት አትመልከት፥ ለጊዜው ጕሮሮህን ያጣፍጣል፥


የአመንዝራ ሴት ክብር እስከ አንዲት እንጀራ ነው፤ አመንዝራ ሴትም የተከበሩ ወንዶች ነፍስን ታጠምዳለች።


ባልንጀራን አትመኑ፥ በወዳጅም አትታመኑ፥ የአፍህን ደጅ በብብትህ ከምትተኛው ጠብቅ።


የኤ​ፍ​ሬ​ምም ሰዎች ተሰ​በ​ሰቡ፤ ወደ ጻፎ​ንም ተሻ​ግ​ረው ዮፍ​ታ​ሔን፥ “ከአ​ሞን ልጆች ጋር ለመ​ዋ​ጋት ስታ​ልፍ ከአ​ንተ ጋር እን​ድ​ን​ሄድ ስለ​ምን አል​ጠ​ራ​ኸ​ንም? ቤት​ህን በአ​ንተ ላይ በእ​ሳት እና​ቃ​ጥ​ለ​ዋ​ለን” አሉት።


እር​ሱም፥ “ከበ​ላ​ተኛ መብል ወጣ፤ ከብ​ር​ቱም ጣፋጭ ወጣ” አላ​ቸው። እስከ ሦስት ቀንም እን​ቆ​ቅ​ል​ሹን መፍ​ታት አል​ቻ​ሉም።


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም፥ “ይህን ያደ​ረገ ማን ነው?” አሉ። እነ​ር​ሱም፥ “ሚስ​ቱን ወስዶ ለሚ​ዜው አጋ​ብ​ቶ​በ​ታ​ልና የቴ​ም​ና​ታ​ዊዉ አማች ሶም​ሶን ነው” አሉ​አ​ቸው። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ወጥ​ተው የአ​ባ​ቷን ቤትና እር​ስ​ዋን አባ​ቷ​ንም በእ​ሳት አቃ​ጠሉ።


የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን መሳ​ፍ​ን​ትም ወደ እር​ስዋ ወጥ​ተው፥ “እር​ሱን አባ​ብ​ለሽ በእ​ርሱ ያለ ታላቅ ኀይል በምን እንደ ሆነ፥ እኛም እር​ሱን ለማ​ዋ​ረድ እና​ስ​ረው ዘንድ የም​ና​ሸ​ን​ፈው በምን እንደ ሆነ ዕወቂ፤ እኛም እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችን ሺህ አንድ መቶ ብር እን​ሰ​ጥ​ሻ​ለን” አሉ​አት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos