1 ቆሮንቶስ 15:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙታን እንዴት ይነሣሉ? የሚነሡስ በምን አካላቸው ነው? የሚል አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን፣ “ሙታን እንዴት ይነሣሉ? የሚመጡትስ በምን ዐይነት አካል ነው?” የሚል ሰው ሊኖር ይችላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን አንዱ፥ “ሙታን እንዴት ይነሣሉ? የሚወጡትስ በምን ዓይነት አካል ነው?” ብሎ ቢጠይቅ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ሰው “የሞቱ ሰዎች የሚነሡት እንዴት ነው? ከሞት ሲነሡ የሚኖራቸው አካልስ ምን ዐይነት ነው?” ብሎ ይጠይቅ ይሆናል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ሰው፦ ሙታን እንዴት ይነሣሉ? በምንስ ዓይነት አካል ይመጣሉ? የሚል ይኖር ይሆናል። |
የነፋስ መንገድ እንዴት እንደ ሆነች፥ አጥንትም በእርጉዝ ሆድ እንዴት እንድትዋደድ እንደማታውቅ፥ እንዲሁም ሁሉን የሚሠራውን የእግዚአብሔርን ሥራ አታውቅም።
እግዚአብሔርም ተናገረኝ፤ እንዲህም አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! እነዚህ አጥንቶች የእስራኤል ቤት ሁሉ ናቸው፤ እነሆ! አጥንቶቻችን ደርቀዋል፤ ተስፋችንም ጠፍቶአል፤ ፈጽመንም ተቈርጠናል ብለዋል።
እርሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! እነዚህ አጥንቶች በሕይወት ይኖራሉን?” አለኝ። እኔም፥ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ታውቃለህ” አልሁ።
ኒቆዲሞስም፥ “ሰው ከሸመገለ በኋላ ዳግመኛ መወለድ እንደምን ይችላል? ዳግመኛ ይወለድ ዘንድ ወደ እናቱ ማኅፀን ተመልሶ መግባት ይችላልን?” አለው።
እርሱም እንደ ከሃሊነቱ ረዳትነት መጠን የተዋረደውን ሥጋችንን የሚያድሰው፥ ክቡር ሥጋዉንም እንዲመስል የሚያደርገው፥ የሚያስመስለውም፥ ሁሉም የሚገዛለት ነው።