Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ቆሮንቶስ 15:35 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 አንድ ሰው “የሞቱ ሰዎች የሚነሡት እንዴት ነው? ከሞት ሲነሡ የሚኖራቸው አካልስ ምን ዐይነት ነው?” ብሎ ይጠይቅ ይሆናል፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 ነገር ግን፣ “ሙታን እንዴት ይነሣሉ? የሚመጡትስ በምን ዐይነት አካል ነው?” የሚል ሰው ሊኖር ይችላል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 ነገር ግን አንዱ፥ “ሙታን እንዴት ይነሣሉ? የሚወጡትስ በምን ዓይነት አካል ነው?” ብሎ ቢጠይቅ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 ሙታን እን​ዴት ይነ​ሣሉ? የሚ​ነ​ሡስ በምን አካ​ላ​ቸው ነው? የሚል አለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 ነገር ግን ሰው፦ ሙታን እንዴት ይነሣሉ? በምንስ ዓይነት አካል ይመጣሉ? የሚል ይኖር ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar




1 ቆሮንቶስ 15:35
13 Referencias Cruzadas  

ሞኝ ሰው ጥበበኛ ከሚሆን ይልቅ የሜዳ አህያ ሰው ሆኖ ቢወለድ ይቀላል።


አንተ ግን ‘እግዚአብሔር ምን ያውቃል? ከድቅድቅ ጨለማ ባሻገር ሆኖ እንዴት ሊፈርድብን ይችላል?


እነርሱም “በውኑ እግዚአብሔር ያውቃልን? ልዑል እግዚአብሔርስ ዕውቀት አለውን?” ይላሉ።


የነፋስን አካሄድና የሰውም ሕይወት አፈጣጠር በእናቱ ማሕፀን እንዴት እንደሚጀመር እንደማታውቅ የሁሉ ነገር ፈጣሪ እግዚአብሔር ሥራውን እንዴት እንደሚያከናውን ማወቅ አትችልም።


እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! የእስራኤል ሕዝብ እኮ ልክ እንደእነዚህ አጥንቶች ናቸው፤ እነርሱ ‘እነሆ፥ አጥንቶቻችን ደርቀዋል፤ ተስፋ ቈርጠናል፤ የእኛ ጉዳይ አልቆለታል’ ይላሉ።


እርሱም “የሰው ልጅ ሆይ! እነዚህ አጥንቶች ዳግመኛ ሕይወት የሚያገኙ ይመስልሃልን?” አለኝ። እኔም “ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! ይህን የምታውቅ አንተ ብቻ ነህ” አልኩት።


ኒቆዲሞስም “ታዲያ፥ ሰው ከሸመገለ በኋላ እንዴት ሊወለድ ይችላል? ዳግመኛ ወደ እናቱ ማሕፀን ገብቶ መወለድ ይችላልን?” ሲል ጠየቀ።


ኒቆዲሞስም “ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?” ሲል ጠየቀው።


ሰዎቹም “ታዲያ፥ ዐይኖችህ እንዴት ተከፈቱ?” አሉት።


ስለዚህ “የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመቃወም ማንም አይችልም፤ ታዲያ፥ እርሱ ሰዎችን በክፉ ሥራቸው ለምን ይወቅሳቸዋል” ብለህ ትጠይቀኝ ይሆናል።


እርሱ ይህን የተዋረደውን ሰውነታችንን በመለወጥ የእርሱን ክቡር ሰውነት እንዲመስል ያደርገዋል፤ ይህንንም የሚያደርገው ሁሉን በሥልጣኑ ሥር ለማድረግ በሚያስችለው ኀይል ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos