እግዚአብሔር ወደ ታች ወደ ሰዎች ይመለከታል፥ ሊመረመሩ የማይችሉ ነገሮችን ሁሉ፥ ቍጥር የሌላቸውን የተከበሩትንና ድንቆችንም ያስተውላል።
1 ቆሮንቶስ 1:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አለን የሚሉትንም ያሳፍር ዘንድ ዘመድ የሌላቸውንና የተናቁትን፥ ከቍጥርም ያልገቡትን እግዚአብሔር መረጠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር የተከበረውን እንደሌለ ለማድረግ፣ በዚህ ዓለም ዝቅ ያለውንና የተናቀውን ነገር፣ ቦታም ያልተሰጠውን ነገር መረጠ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም የሆነውን ነገር እንዲያጠፋ የዓለምን ምናምንቴ እና የተናቀውን ነገር፥ ያልሆነውንም ነገር መረጠ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በዓለም ሰዎች ዘንድ አሉ ተብለው የሚታዩትን ነገሮች እንደሌሉ ለማድረግ በዓለም የተዋረደና የተናቀ ከንቱም መስሎ የሚታየውን ነገር መረጠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም የሆነውን ነገር እንዲያጠፋ የዓለምን ምናምንቴ ነገር የተናቀውንም ነገር ያልሆነውንም ነገር መረጠ፥ |
እግዚአብሔር ወደ ታች ወደ ሰዎች ይመለከታል፥ ሊመረመሩ የማይችሉ ነገሮችን ሁሉ፥ ቍጥር የሌላቸውን የተከበሩትንና ድንቆችንም ያስተውላል።
እግዚአብሔር የአሕዛብን ምክር ይመልሳል፥ የሕዝቡንም ዐሳብ ይመልሳል። የአለቆችን ምክራቸውን ያስረሳቸዋል።
የትዕቢተኞች ሰዎች ዐይኖች ይዋረዳሉ፤ የሰዎችም ኵራት ትወድቃለች፥ በዚያም ቀን እግዚአብሔር ብቻ ከፍ ከፍ ይላል።
የእግዚአብሔርም መልአክ ወጣ፤ ከአሦራውያንም ሰፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ሰዎችን ገደለ፤ ማለዳም በተነሡ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሁሉም በድኖች ሆነው አገኙአቸው።
“ለብዙዎች አሕዛብ አባት አደርግሃለሁ” ተብሎ እንደ ተጻፈ ሙታንን በሚያስነሣቸው፥ የሌሉትንም እንደ አሉ በሚያደርጋቸው በአመነበት በእግዚአብሔር ፊት አብርሃም የሁላችን አባት ነው።
እንግዲህ ጥበበኛ ማን ነው? ጸሓፊስ ማን ነው? ይህን ዓለምስ የሚመረምረው ማን ነው? እግዚአብሔር የዚህን ዓለም ጥበብ ስንፍና አላደረገውምን?
ለዐዋቆች ጥበብን እንነግራቸዋለን፤ ነገር ግን የዚህን ዓለም ጥበብ ወይም ያልፉ ዘንድ ያላቸውን የዚህን ዓለም ሹሞች ጥበብ አይደለም።
እነሆ እናንተ ስላገበራችሁኝ በመመካቴ ሰነፍ ሆንሁ፤ ለእኔማ በእናንተ ዘንድ ልከብርና እናንተም ምስክሮች ልትሆኑኝ ይገባኝ ነበር፤ እኔ እንደ ኢምንት ብሆንም ዋናዎቹ ሐዋርያት ሁሉ ከሠሩት ሥራ ያጐደልሁባችሁ የለምና።
እግዚአብሔርም በጎ ያደርግልህ ዘንድ፥ ያበዛህም ዘንድ ደስ ይለው እንደ ነበረ፥ እንዲሁ እግዚአብሔር ሲያጠፋህ፥ ሲያፈርስህም ደስ ይለዋል፤ ትወርሳትም ዘንድ ከምትገባባት ምድር ትነቀላለህ ።
ልጆች በሥጋና በደም አንድ ናቸውና፤ እርሱ ደግሞ በዚህ ከእነርሱ ጋር አንድ ሆነ፤ ለእነርሱም እንደ ወንድም ሆነላቸው፤ መልአከ ሞትን በሞቱ ይሽረው ዘንድ፥ ይኸውም ሰይጣን ነው።