1 ቆሮንቶስ 1:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን የእስጢፋኖስን ቤተ ሰብእ አጥምቄአለሁ፤ እንግዲህ ሌላም ያጠመቅሁት እንዳለ አላውቅም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በርግጥ የእስጢፋኖስንም ቤተ ሰው አጥምቄአለሁ፤ ከእነዚህ ሌላ ግን ማጥመቄ ትዝ አይለኝም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስጢፋኖስንም ቤተ ሰዎች ደግሞ አጥምቄአለሁ፤ ከነዚህ ሌላ አጥምቄ እንደሆነ አላውቅም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (እርግጥ ነው፤ የእስጢፋኖስንም ቤተሰብ አጥምቄአለሁ፤ ከነዚህ ሌላ እኔ ያጠመቅሁት ሰው መኖሩን አላስታውስም፤) መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስጢፋኖስንም ቤተ ሰዎች ደግሞ አጥምቄአለሁ፤ ጨምሬ ሌላ አጥምቄ እንደ ሆነ አላውቅም። |
እርስዋም ከቤተ ሰቦችዋ ጋር ተጠመቀች፤ “ለእግዚአብሔር አማኝ ካደረጋችሁኝስ ወደ ቤቴ ገብታችሁ እደሩ” ብላ ማለደችን፤ የግድም አለችን።
ወንድሞቻችን ሆይ፥ የእስጢፋኖስና የፈርዶናጥስ፥ የአካይቆስም ቤተሰቦች፥ የአካይያ መጀመሪያዎች እንደ ሆኑ፥ ቅዱሳንንም ለማገልገል ራሳቸውን እንደ ሰጡ ታውቁ ዘንድ እማልዳችኋለሁ።
እስጢፋኖስ፥ ፈርዶናጥስና አካይቆስ በመምጣታቸውም ደስ ይለኛል፤ እናንተ ያጐደላችሁትን እነርሱ ፈጽመዋልና።