ለእግዚአብሔርም ቤት አገልግሎት የምስክሩን ድንኳን ሥርዐት፥ የወንድሞቻቸውን የአሮንን ልጆች ሥርዐት ለመጠበቅ ሹሞአቸው ነበር።
1 ዜና መዋዕል 9:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱና ልጆቻቸውም በእግዚአብሔር ቤት በድንኳኑ ደጆች ላይ በረኞች ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የማደሪያውን ድንኳን፣ ማለትም የእግዚአብሔርን ቤት የሚጠብቁትም እነርሱና ዘሮቻቸው ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱና ልጆቻቸውም በጌታ ቤት በድንኳኑ ደጆች ላይ ዘበኞች ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱና ልጆቻቸው የእግዚአብሔር ቅጽር በሮችን መጠበቃቸውን ቀጠሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱና ልጆቻቸውም በእግዚአብሔር ቤት በድንኳኑ ደጆች ላይ ዘበኞች ነበሩ። |
ለእግዚአብሔርም ቤት አገልግሎት የምስክሩን ድንኳን ሥርዐት፥ የወንድሞቻቸውን የአሮንን ልጆች ሥርዐት ለመጠበቅ ሹሞአቸው ነበር።
እንደ ወንድሞቻቸው ሆነው በእግዚአብሔር ቤት ያገለግሉ ዘንድ የበረኞች አለቆች በየሰሞናቸው የሚጠብቁ እነዚህ ነበሩ።
የመድረኩ በረኞች ይሆኑ ዘንድ የተመረጡ እነዚህ ሁሉ ሁለት መቶ ዐሥራ ሁለት ነበሩ። እነዚህ በመንደሮቻቸው በየትውልዳቸው ተቈጠሩ። ዳዊትና ነቢዩ ሳሙኤል ታማኝነታቸውን አይተው በሥራቸው አቆሙአቸው።
እነርሱም መዘምራኑና በረኞቹም የአምላካቸውን ሥርዐት የመንጻታቸውን ሥርዐት እንደ ዳዊትና እንደ ልጁ እንደ ሰሎሞን ትእዛዝ ጠበቁ።