1 ዜና መዋዕል 9:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በነጦፋውያንም መንደሮች የተቀመጠው የሕልቃና ልጅ የአሳ ልጅ በራክያ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኤዶታም ልጅ፣ የጋላል ልጅ፣ የሰሙስ ልጅ አብድያ። እንዲሁም በነጦፋውያን ከተሞች የኖረው የሕልቃና ልጅ፣ የአሳ ልጅ በራክያ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የኤዶታም ልጅ የጋላል ልጅ የሰሙስ ልጅ አብድያ ነበር፤ በነጦፋውያንም መንደሮች የተቀመጠው የሕልቃና ልጅ የአሳ ልጅ በራክያ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኤዶታም ልጅ የጋላል ልጅ የሰሙስ ልጅ አብድያ፤ በነጦፋውያንም መንደሮች የተቀመጠው የሕልቃና ልጅ የአሳ ልጅ በራክያ። |
ዳዊትና የሠራዊቱ አለቆችም ከአሳፍና ከኤማን ከኤዶትምም ልጆች በመሰንቆና በበገና፥ በጸናጽልም የሚዘምሩ ሰዎችን ለማገልገል ለዩ፤ በየአገልግሎታቸውም ሥራ የሚሠሩ ሰዎች ቍጥር ይህ ነበረ።
ከኤዶትም የኤዶትም ልጆች፤ ጎዶልያስ፥ ሱሪ፥ የሻያ፥ ሰሜኢ፥ ሐሸብያ፥ መታትያ፥ እነዚህ ስድስቱ ከአባታቸው ከኤዶትም ጋር በበገና እየዘመሩ እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር።
እነዚህ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት በጸናጽልና በበገና፥ በመሰንቆም ከአባታቸው ጋራ የእግዚአብሔርን ቤት ለማገልገል ወደ ንጉሡ ቀርበው ያመሰግኑ ነበር። አሳፍም ኤዶትምም ኤማንም ያመሰግኑ ነበር።
በቀባቃር፥ ኤሬስ፥ ጋላል፥ የአሳፍ ልጅ የዝክሪ ልጅ የሜካ ልጅ ማታንያስ፤ የኤዶታም ልጅ የጋላል ልጅ የሰማያ ልጅ አብድያ፤
የአሳፍም ልጆች መዘምራን እንደ ዳዊት፥ እንደ አሳፍም፥ እንደ ኤማንም የንጉሡም ባለ ራእይ እንደ ነበረው እንደ ኤዶትም ትእዛዝ በየስፍራቸው ነበሩ፤ በረኞቹም በሮቹን ሁሉ ይጠብቁ ነበር፤ ወንድሞቻቸውም ሌዋውያን ያዘጋጁላቸው ነበርና ከአገልግሎታቸው ይርቁ ዘንድ አያስፈልጋቸውም ነበር።
በጸሎትም ጊዜ ምስጋናን የሚጀምሩ አለቃው የአሳፍ ልጅ፥ የዛብዲ ልጅ፥ የሚካ ልጅ ማታንያ፥ በወንድሞቹም መካከል ሁለተኛ የነበረ ቦቂቦቅያ፥ የኢዶትም ልጅ፥ የጌላል ልጅ፥ የሰሙዓ ልጅ አብድያ።