1 ዜና መዋዕል 8:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሪዓ፥ ሰማዕ ነበሩ፤ እነርሱም የጌትን ነዋሪዎች ያሳደዱ የኤሎን ሰዎች የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ነበሩ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኤሎን ይኖሩ ለነበሩ ቤተ ሰቦች አለቆችና የጋት ነዋሪዎችን አስወጥተው ያሳደዱ በሪዓና ሽማዕ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሪዓና ሽማዕ የጌትን ሰዎች ያሳደዱ የኤሎን ሰዎች የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ነበሩ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሪዓና ሴማዕ በአያሎን ከተማ ለሰፈሩት ቤተሰቦች አለቆች ነበሩ፤ እነርሱም በጋት ከተማ የሚኖረውን ሕዝብ አባረሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሪዓ፥ ሽማዕ፥ የጌትን ሰዎች ያሳደዱ የኤሎን ሰዎች የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ነበሩ፤ |
ያን ጊዜም እግዚአብሔር በእስራኤል ልጆች እጅ አሞሬዎናውያንን አሳልፎ ሰጠ፤ እርሱ በገባዖን እነርሱን ባጠፋበት፥ እነርሱም ከእስራኤል ልጆች ፊት በጠፉበት ቀን ኢያሱ ከእግዚአብሔር ጋር ተነጋገረ፤ እንዲህም አለ፥ “በገባዖን ላይ ፀሐይ ትቁም፤ በኢሎንም ሸለቆ ጨረቃ፤”