የኤዜራስም ልጆች፤ ኢያቴር፥ ሞራድ፥ ጋፌር፥ ኢያሎን ነበሩ፤ ኢያቴርም ማሮንን፥ ሰማዒን፥ የኢስቲሞንን አባት ይስባኤልን ወለደ።
1 ዜና መዋዕል 6:57 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለአሮንም ልጆች የመማፀኛውን ከተሞች፥ ኬብሮንን፥ ልብናንና መሰማርያዋን፥ ሴልናንና መሰማሪያዋን፤ ኤስትሞዓንና መሰማሪያዋን ሰጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለአሮን ዘሮች የመማፀኛ ከተሞች የሆኑትን ኬብሮንን፣ ልብናን፣ የቲርን፣ ኤሽትሞዓን፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለአሮንም ልጆች እነዚህን የመማፀኛ ከተሞች ሰጡ፤ እርሱም፦ ኬብሮን፥ ልብናና መሰማሪያዋ፥ ደግሞ የቲር፥ ኤሽትሞዓና መሰማሪያዋ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለአሮን ልጆች የተመደቡ ከተሞች፥ የመማጠኛ ከተማ የሆነችው ኬብሮን፥ ያቲር፥ ሊብና፥ ኤሽተሞዓ፥ ሒሌን፥ ደቢር፥ ዐሻንና ቤትሼሜሽ ሲሆኑ የግጦሽ ቦታዎቻቸውንም ይጨምራል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለአሮንም ልጆች የመማፀኛውን ከተሞች፥ ኬብሮንን፥ ልብናንና መሰምርያዋን፥ ደግሞ የቲርን፥ ኤሽትሞዓንና መሰማርያዋን፥ |
የኤዜራስም ልጆች፤ ኢያቴር፥ ሞራድ፥ ጋፌር፥ ኢያሎን ነበሩ፤ ኢያቴርም ማሮንን፥ ሰማዒን፥ የኢስቲሞንን አባት ይስባኤልን ወለደ።
ከይሁዳም ልጆች ነገድ፥ ከስምዖንም ልጆች ነገድ፥ ከብንያምም ልጆች ነገድ፥ እነዚህን በስማቸው የተጠሩትን ከተሞች በዕጣ ሰጡ።