1 ዜና መዋዕል 22:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም፥ እነሆ፥ በድህነቴ ለእግዚአብሔር ቤት መቶ ሺህ መክሊት ወርቅና አንድ ሚሊዮን መክሊት ብር፥ ሚዛንም የሌላቸው ብዙ ናስና ብረት አዘጋጅቻለሁ፤ ደግሞም የማይቈጠር ብዙ የዝግባ እንጨትና ድንጋዮች አዘጋጅቻለሁ፤ አንተም ልጄ ከዚያ በላይ ጨምር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ለእግዚአብሔር ቤት እንዲሆንም አንድ ሺሕ መክሊት ወርቅ፣ አንድ ሚሊዮን መክሊት ብር፣ ከብዛቱ የተነሣ ሊመዘን የማይቻል ናስና ብረት ለማዘጋጀት በተቻለኝ ሁሉ ጥሬአለሁ፤ በተረፈ አንተ ጨምርበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም፥ እነሆ፥ በድህነቴ ለጌታ ቤት መቶ ሺህ መክሊት ወርቅና አንድ ሚሊዮን መክሊት ብር፥ በሚዛንም የማይመዘን ብዙ ናስና ብረት አዘጋጀሁ፤ ደግሞም እንጨትና ድንጋዮች አዘጋጀሁ፥ አንተም በዚያ ላይ ጨምርበት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለ ቤተ መቅደሱ ሥራ የሆነ እንደሆን፥ በበኩሌ ለሕንጻ ሥራ የሚውል ሦስት ሺህ አራት መቶ ቶን ወርቅና ከሠላሳ አራት ሺህ ቶን በላይ የሚሆን ብር አከማችቼልሃለሁ፤ በተጨማሪም ስፍር ቊጥር የሌለው ነሐስና ብረት አዘጋጅቼልሃለሁ፤ እንዲሁም እንጨትና ድንጋይ አዘጋጅቼልሃለሁ፤ ይሁን እንጂ አንተም በተጨማሪ ማግኘት አለብህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም፥ እነሆ በምችለው ለእግዚአብሔር ቤት መቶ ሺህ መክሊት ወርቅና አንድ ሚሊዮን መክሊት ብር፥ ሚዛንም የሌላቸው ብዙ ናስና ብረት አዘጋጀሁ፤ ደግሞም እንጨትና ድንጋዮች አዘጋጀሁ፤ አንተም ከዚያ በላይ ጨምር። |
ሰሎሞንም ለእግዚአብሔር ቤት የሠራቸውን ሁለቱን ዓምዶች፥ አንዱንም ኵሬ መቀመጫዎቹንም ወሰደ፤ ለእነዚህም ዕቃዎች ሁሉ ናስ ሚዛን አልነበረውም።
አንተም ብዙ ሠራተኞችን፥ ድንጋይና እንጨት ወቃሪዎችንና ጠራቢዎችን፥ ሥራውንም ሁሉ ለማድረግ ጠቢባን ሰዎችን አብዝተህ ጨምር።
እኔም እንደ ጉልበቴ ሁሉ ለአምላኬ ለእግዚአብሔር ቤት ወርቅን፥ ብርን፥ ናስን፥ ብረትን፥ እንጨትን፥ ደግሞም መረግድንና በፈርጥ የሚገባ ድንጋይን፥ የሚለጠፍ ድንጋይን፥ ልዩ ልዩ መልክ ያለውንም ድንጋይ፥ የከበረውንም ድንጋይ ከየዓይነቱ፥ ብዙም እብነ በረድ አዘጋጅቻለሁ።
ንጉሡ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤት ያሠራቸውን ሁለቱን ዐምዶች፥ አንዱንም ኵሬ፥ ከመቀመጫዎቹም በታች የነበሩትን ዐሥራ ሁለቱን የናስ በሬዎች ወሰደ፤ ለእነዚህ የናስ ዕቃዎች ሁሉ ሚዛን አልነበራቸውም።
እያንዳንዱም የብር ወጭት መቶ ሠላሳ ሰቅል፥ እያንዳንዱም ድስት ሰባ ሰቅል ነበረ፤ የዚህም ዕቃ ሁሉ ብር በመቅደሱ ሰቅል ሚዛን ሁለት ሺህ አራት መቶ ሰቅል ነበረ።
በብዙ መከራ ከመፈተናቸው የተነሣ ደስታቸው በዝቶአልና፤ በድህነታቸው ጥልቅነትም የለጋስነታቸው ባለጠግነት በዝታለችና።