እርሱም፥ “መንግሥቱ ለእኔ እንደ ነበረ፥ እስራኤልም ሁሉ ንጉሥ እሆን ዘንድ ፊታቸውን ወደ እኔ አድርገው እንደ ነበረ አንቺ ታውቂያለሽ፤ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ሆኖለታልና መንግሥት ተመልሳ ለወንድሜ ሆናለች።
1 ዜና መዋዕል 22:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ ለስሜ ቤት ይሠራል፤ ልጅም ይሆነኛል፤ እኔም አባት እሆነዋለሁ፤ የመንግሥቱንም ዙፋን በእስራኤል ላይ ለዘለዓለም አጸናለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለስሜ ቤት የሚሠራልኝ እርሱ ነው። እርሱ ልጅ ይሆነኛል፤ እኔም አባት እሆነዋለሁ። ዙፋኑንም በእስራኤል ላይ ለዘላለም አጸናለሁ።’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ ለስሜ ቤት ይሠራል፥ ልጅም ይሆነኛል፥ እኔም አባት እሆነዋለሁ፤ የመንግሥቱንም ዙፋን በእስራኤል ላይ ለዘለዓለም አጸናለሁ።’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእኔ ቤተ መቅደስ የሚሠራልኝ እርሱ ነው፤ እርሱ ልጅ ይሆነኛል፤ እኔም አባት እሆነዋለሁ፤ መንግሥቱም በእስራኤል ላይ ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ ለስሜ ቤት ይሠራል፤ ልጅም ይሆነኛል፤ እኔም አባት እሆነዋለሁ፤ የመንግሥቱንም ዙፋን በእስራኤል ላይ ለዘላለም አጸናለሁ።’ |
እርሱም፥ “መንግሥቱ ለእኔ እንደ ነበረ፥ እስራኤልም ሁሉ ንጉሥ እሆን ዘንድ ፊታቸውን ወደ እኔ አድርገው እንደ ነበረ አንቺ ታውቂያለሽ፤ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ሆኖለታልና መንግሥት ተመልሳ ለወንድሜ ሆናለች።
አሁንም ያጸናኝ፥ በአባቴም በዳዊት ዙፋን ላይ ያስቀመጠኝ፥ እንደ ተናገረውም ቤትን የሠራልኝ ሕያው እግዚአብሔርን! ዛሬ አዶንያስ ፈጽሞ ይገደላል።
እነሆም፥ እግዚአብሔር ለአባቴ ለዳዊት፦ በአንተ ፋንታ በዙፋንህ ላይ የማስቀምጠው ልጅህ እርሱ ለስሜ ቤት ይሠራል ብሎ እንደ ነገረው፥ ለአምላኬ ለእግዚአብሔር ስም ቤት እሠራ ዘንድ አስባለሁ።
እኔ፦ በእስራኤል ላይ የሚገዛ ሰውን ከአንተ አላጠፋም ብዬ ለአባትህ ለዳዊት እንደ ተናገርሁ፥ የመንግሥትህን ዙፋን በእስራኤል ላይ ለዘለዓለም አጸናለሁ።
እግዚአብሔርም ብዙ ልጆች ሰጥቶኛልና ከልጆቼ ሁሉ በእግዚአብሔር መንግሥት ዙፋን ላይ ተቀምጦ በእስራኤል ላይ ይነግሥ ዘንድ ልጄን ሰሎሞንን መርጦታል።
ለባሪያህ ለአባቴ ለዳዊት እንዲህ ብለህ የተናገርኸውን የጠበቅህ፥ በአፍህ ተናገርህ፤ ዛሬም እንደ ሆነው በእጆችህ ፈጸምኸው።
ለአለቆች ሰላምን ለእርሱም ሕይወትን አመጣለሁና፤ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም ድረስ በፍርድና በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ ግዛቱ ታላቅ ይሆናል፤ በዳዊት ዙፋን መንግሥቱ ትጸናለች፤ ለሰላሙም ፍጻሜ የለውም። የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቅንዐት ይህን ያደርጋል።
ከመላእክትስ ከሆነ ጀምሮ፥ “አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወለድሁህ” ዳግመኛም፥ “እኔ አባት እሆነዋለሁ እርሱም ልጄ ይሆነኛል” ያለው ከቶ ለማን ነው?