እነዚህም በጌት ውስጥ ከኀያላን የተወለዱ ነበሩ፤ እነርሱም አራት ኀያላን ነበሩ፤ በዳዊትም እጅ በአገልጋዮቹም እጅ ወደቁ።
1 ዜና መዋዕል 21:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያንጊዜም ሰይጣን በእስራኤል ላይ ተነሣ፤ እስራኤልንም ይቈጥር ዘንድ ዳዊትን አነሣሣው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰይጣን በእስራኤል ላይ ተነሥቶ ዳዊት የእስራኤልን ሕዝብ እንዲቈጥር አነሣሣው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰይጣንም በእስራኤል ላይ ተነሣ፥ እስራኤልንም እንዲቈጥር ዳዊትን አነሣሣው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰይጣን በእስራኤል ሕዝብ ላይ ተነሥቶ ዳዊትን የሕዝብ ቈጠራ እንዲያደርግ አነሣሣው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰይጣንም በእስራኤል ላይ ተነሣ፤ እስራኤልንም ይቈጥር ዘንድ ዳዊትን አነሣሣው። |
እነዚህም በጌት ውስጥ ከኀያላን የተወለዱ ነበሩ፤ እነርሱም አራት ኀያላን ነበሩ፤ በዳዊትም እጅ በአገልጋዮቹም እጅ ወደቁ።
የሶርህያ ልጅ ኢዮአብም መቍጠር ጀመረ፤ ነገር ግን አልፈጸመም፤ ስለዚህ ነገር በእስራኤል ላይ ቍጣ ሆነ፤ ቍጥራቸውም በንጉሡ በዳዊት የታሪክ መጽሐፍ አልተጻፈም።
እነዚህ ሁሉ የአሴር ልጆች፥ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች፥ የተመረጡ ጽኑዓን ኀያላን ሰዎች፥ የመኳንንቱ አለቆች ነበሩ። በትውልዳቸውም በሰልፍ ለመዋጋት የተቈጠሩ ሃያ ስድስት ሺህ ሰዎች ነበሩ።
ከዕለታት አንድ ቀን እንዲህ ሆነ፤ የእግዚአብሔር መላእክት መጥተው በእግዚአብሔር ፊት ቆሙ፥ ሰይጣን ደግሞ በእግዚአብሔር ፊት ለመቆም ከእነርሱ ጋር መጣ።
“አንተ የእስራኤልን ልጆች ቍጥር የወሰድህ እንደ ሆነ በቈጠርሃቸው ጊዜ መቅሠፍት እንዳይሆንባቸው፥ በቈጠርሃቸው ጊዜ ከእነርሱ ሰው ሁሉ እንደ ቍጥራቸው መጠን የነፍሱን ቤዛ ለእግዚአብሔር ይስጥ።
ጴጥሮስም፥ “ሐናንያ ሆይ፥ መንፈስ ቅዱስን ታታልለው ዘንድ፥ የመሬትህንም ዋጋ ከፍለህ ታስቀር ዘንድ ሰይጣን በልብህ እንዴት አደረ?
ታላቅም ድምፅ በሰማይ ሰማሁ፤ እንዲህ ሲል “አሁን የአምላካችን ማዳንና ኀይል መንግሥትም የክርስቶስም ሥልጣን ሆነ፤ ቀንና ሌሊትም በአምላካችን ፊት የሚከሳቸውየወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአልና።