1 ዜና መዋዕል 2:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያም በኋላ ኤስሮም ስድሳ ዓመት በሆነው ጊዜ ወደ አገባት ወደ ገለዓድ አባት ወደ ማኬር ልጅ ገባ፤ ሴጉብንም ወለደችለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም በኋላ ኤስሮም ስድሳ ዓመት ሲሆነው የገለዓድን አባት የማኪርን ልጅ አገባ፤ እርሷም ሠጉብን ወለደችለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም በኋላ ኤስሮም ስልሳ ዓመት በሆነው ጊዜ ወዳገባት ወደ ገለዓድ አባት ወደ ማኪር ልጅ ገባ፤ ሠጉብንም ወለደችለት። ሠጉብም ኢያዕርን ወለደ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሔጽሮን ሥልሳ ዓመት ሲሞላው የገለዓድ እኅት የነበረችውን የማኪርን ልጅ አግብቶ ሰጉብ የተባለውን ወንድ ልጅ ወለደ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚያም በኋላ ኤስሮም ስድሳ ዓመት በሆነው ጊዜ ወዳገባት ወደ ገለዓድ አባት ወደ ማኪር ልጅ ገባ፤ ሠጉብንም ወለደችለት። |
ከዮሴፍ ልጅ ከምናሴ ወገን ፥ የምናሴ ልጅ፥ የማኪር ልጅ፥ የገለአድ ልጅ፥ የኦፌር ልጅ፥ የሰለጰዓድ ሴቶች ልጆች መጡ፤ የእነዚህም ሴቶች ልጆች ስሞች መሐላ፥ ኑኃ፥ ሄግላ፥ ሚልካ፥ ቴርሳ ነበሩ።