የእግዚአብሔርንም ታቦት አምጥተው ዳዊት በተከለላት ድንኳን ውስጥ በስፍራዋ አኖሩአት፤ ዳዊትም የሚቃጠልና የሰላም መሥዋዕትን በእግዚአብሔር ፊት አሳረገ።
1 ዜና መዋዕል 17:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቤን እስራኤልን ከግብፅ ምድር ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በድንኳንና በማደሪያ ኖርሁ እንጂ በቤት ውስጥ አልኖርሁም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤልን ከግብጽ ምድር ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፣ ከአንዱ ድንኳን ወደ ሌላው ድንኳን፣ ከአንዱ ማደሪያ ወደ ሌላው ማደሪያ እሄድ ነበር እንጂ፣ በቤት ውስጥ አልተቀመጥሁም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤልን ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ከድንኳን ወደ ድንኳን፥ ከማደሪያም ወደ ማደሪያ እሄድ ነበር እንጂ በቤት ውስጥ አልኖርሁምና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤልን ሕዝብ ከግብጽ ባርነት ነጻ ካወጣሁበት ጊዜ አንሥቶ እስከ አሁን ድረስ በቤተ መቅደስ ውስጥ ኖሬ አላውቅም፤ ዘወትር በድንኳን ውስጥ ሆኜ ከቦታ ወደ ቦታ እዘዋወር ነበር፤ |
የእግዚአብሔርንም ታቦት አምጥተው ዳዊት በተከለላት ድንኳን ውስጥ በስፍራዋ አኖሩአት፤ ዳዊትም የሚቃጠልና የሰላም መሥዋዕትን በእግዚአብሔር ፊት አሳረገ።
የእስራኤልን ልጆች ከግብፅ ምድር ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በድንኳንና በማደሪያ እሄድና እመላለስ ነበር እንጂ በቤት አልተቀመጥሁምና፥
ሕዝቤን እስራኤልን ከግብፅ ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ ስሜ በዚያ ይሆን ዘንድ በእርስዋም ቤት ይሠራልኝ ዘንድ፥ ከእስራኤል ነገድ ሁሉ ከተማን አልመረጥሁም፤ አሁን ግን ስሜ በዚያ ይሆን ዘንድ ኢየሩሳሌምን መርጫለሁ፤ በሕዝቤም በእስራኤል ላይ ንጉሥ ይሆን ዘንድ ዳዊትን መርጫለሁ።”
“በውኑ እግዚአብሔር ከሰው ጋር በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ ሰማይ ከሰማያትም በላይ ያለው ሰማይ ይይዝህ ዘንድ አይችልም፤ ይልቁንስ እኔ ለስምህ የሠራሁት ቤት እንዴት ያንስ!
ነገር ግን ሰማይና ከሰማያት በላይ ያለ ሰማይ ክብሩን ይሸከም ዘንድ አይችልምና ለእርሱ ቤት ይሠራ ዘንድ ማን ይችላል? በፊቱ ዕጣን ከማጠን በቀር ቤት እሠራለት ዘንድ እኔ ማን ነኝ?
“በውኑ እግዚአብሔር ከሰው ጋር በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ፥ ሰማይ ሰማየ ሰማያትም ይወስንህ ዘንድ አይችልም፤ እንግዲያስ እኔ የሠራሁት ይህ ቤት ምንድን ነው?
እርሱ፦ ሕዝቤን ከግብፅ ምድር ካወጣሁበት ጊዜ ጀምሮ ከእስራኤል ነገድ በዚያ ለስሜ ቤት ይሠራበት ዘንድ ከተማን አልመረጥሁም። በሕዝቤ እስራኤል ላይም ይነግሥ ዘንድ ሰውን አልመረጥሁም።
ነገር ግን ስሜ በዚያ እንዲጠራባት ኢየሩሳሌምን መርጫለሁ። በሕዝቤም በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንዲሆን ዳዊትን መርጫለሁ ብሎአል።