1 ዜና መዋዕል 17:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር እርሱ የእስራኤል አምላክ ነው፤ በእውነት የእስራኤል አምላክ ነው ይባል ዘንድ ስምህ ለዘለዓለም ጽኑና ታላቅ ይሁን፤ የአገልጋይህም የዳዊት ቤት በፊትህ የጸና ይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም ስምህ ጸንቶ እንዲኖርና ለዘላለምም ታላቅ እንዲሆን ነው። ከዚያም ሰዎች ‘የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የእስራኤል አምላክ ነው!’ ይላሉ፤ የባሪያህ የዳዊትም ቤት በፊትህ የጸና ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስምህ፦ ‘የሠራዊት ጌታ እርሱ የእስራኤል አምላክ ነው፥ በእውነት የእስራኤል አምላክ ነው’ በሚለው ውስጥ ለዘለዓለም ጽኑና ታላቅ ይሆናል፤ የባርያህም የዳዊት ቤት በፊትህ ጸንቶአል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም የምታደርገው ስምህ ለዘለዓለም የገነነ ይሆን ዘንድና ሰዎችም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የእስራኤል አምላክ ነው እንዲሉ ነው፤ የእኔ የአገልጋይህ ቤትም በፊትህ የጸና ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ‘የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እርሱ የእስራኤል አምላክ ነው፤ በእውነት የእስራኤል አምላክ ነው፤’ ይባል ዘንድ ስምህ ለዘላለም ጽኑና ታላቅ ይሁን፤ የባሪያህም የዳዊት ቤት በፊትህ ጸንቶአል። |
አምላኬ ሆይ፥ ቤት እንድትሠራለት ለባሪያህ በጆሮው ገልጠሃልና ስለዚህ አገልጋይህ ወደ አንተ ይጸልይ ዘንድ ባለሟልነትን አገኘ።
አንተ በማደሪያህ በሰማይ ስማ፤ የምድርም አሕዛብ ሁሉ ስምህን ያውቁ ዘንድ፥ እንደ ሕዝብህም እንደ እስራኤል ይፈሩህ ዘንድ፥ በዚህም በሠራሁት ቤት ስምህ እንደ ተጠራ ያውቁ ዘንድ፥ እንግዳው የሚለምንህን ሁሉ አድርግ።
ኤርምያስም ሴዴቅያስን፥ “የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ ባቢሎን ንጉሥ አለቆች ብትወጣ፥ ነፍስህ በሕይወት ትኖራለች፤ ይህችም ከተማ በእሳት አትቃጠልም፤ አንተም፥ ቤትህም በሕይወት ትኖራላችሁ።
ጌታችን ኢየሱስም ይህን ነገር ተናግሮ ዐይኖቹን ወደ ሰማይ አነሣና እንዲህ አለ፥ “አባት ሆይ፥ ሰዓቱ ደርሶአልና ልጅህ ያከብርህ ዘንድ ልጅህን አክብረው፤
አሁን ግን፥ በሰማያት ያለችውን የምትበልጠውን ሀገር ተስፋ ያደርጉ እንደ ነበር ታወቀ፤ ስለዚህም እግዚአብሔር አምላካቸው ተብሎ ይጠራ ዘንድ በእነርሱ አያፍርም፤ ተስፋ ያደረጉአትን ሀገር አዘጋጅቶላቸዋልና።
ከእነዚያ ዘመናት በኋላ ለቤተ እስራኤል የምገባው ቃል ይህ ነው፦ ሕጌን በልባቸው አሳድራለሁ፤ በሕሊናቸውም እጽፈዋለሁ፤ አምላክ እሆናቸዋለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆኑኛል ይላል እግዚአብሔር።
ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ የሚያገለግልም ቢሆን፥ “እግዚአብሔር በሚሰጠኝ ኀይል ነው” ብሎ ያገልግል፤ ክብርና ሥልጣን እስከ ዘላለም ድረስ ለእርሱ በሚሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።
ታላቅም ድምፅ ከሰማይ “እነሆ የእግዚአብሔር ድንኳን በሰዎች መካከል ነው፤ ከእነርሱም ጋር ያድራል፤ እነርሱም ሕዝቡ ይሆናሉ፤ እግዚአብሔርም እርሱ ራሱ ከእነርሱ ጋር ሆኖ አምላካቸው ይሆናል፤