እነሆም፥ እግዚአብሔር ለአባቴ ለዳዊት፦ በአንተ ፋንታ በዙፋንህ ላይ የማስቀምጠው ልጅህ እርሱ ለስሜ ቤት ይሠራል ብሎ እንደ ነገረው፥ ለአምላኬ ለእግዚአብሔር ስም ቤት እሠራ ዘንድ አስባለሁ።
1 ዜና መዋዕል 17:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ ቤትን ይሠራልኛል ፤ ዙፋኑንም ለዘለዓለም አጸናለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቤት የሚሠራልኝም እርሱ ነው፤ እኔም ዙፋኑን ለዘላለም አጸናለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ ቤት ይሠራልኛል፤ ዙፋኑንም ለዘለዓለም አጸናለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቤተ መቅደስ የሚሠራልኝም እርሱ ይሆናል፤ ዙፋኑንም ለዘለዓለም የጸና እንዲሆን አደርጋለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ ቤት ይሠራልኛል፤ ዙፋኑንም ለዘላለም አጸናለሁ። |
እነሆም፥ እግዚአብሔር ለአባቴ ለዳዊት፦ በአንተ ፋንታ በዙፋንህ ላይ የማስቀምጠው ልጅህ እርሱ ለስሜ ቤት ይሠራል ብሎ እንደ ነገረው፥ ለአምላኬ ለእግዚአብሔር ስም ቤት እሠራ ዘንድ አስባለሁ።
ወደ አባቶችህም ትሄድ ዘንድ ዕድሜህ በተፈጸመ ጊዜ ከአብራክህ የተወለደ ዘርህን ከአንተ በኋላ አስነሣለሁ ፤ መንግሥቱንም አጸናለሁ።
እኔም አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጄ ይሆነኛል፤ ከአንተ አስቀድሞ ከነበሩት እንዳራቅሁ፥ ምሕረቴን ከእርሱ አላርቅም።
እንደዚህም ብለው መለሱልን፦ እኛ የሰማይና የምድር አምላክ ባሪያዎች ነን፥ ከብዙም ዘመን ጀምሮ ተሠርቶ የነበረውን፥ ታላቁም የእስራኤል ንጉሥ ሠርቶ ፈጽሞላቸው የነበረውን ቤት እንሠራለን።
ለአለቆች ሰላምን ለእርሱም ሕይወትን አመጣለሁና፤ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም ድረስ በፍርድና በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ ግዛቱ ታላቅ ይሆናል፤ በዳዊት ዙፋን መንግሥቱ ትጸናለች፤ ለሰላሙም ፍጻሜ የለውም። የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቅንዐት ይህን ያደርጋል።