“ወደ ታላቁ ካህን ወደ ኬልቅዩ ወጥተህ ደጃፉን የሚጠብቁ ከሕዝቡ የሰበሰቡትን ወደ እግዚአብሔር ቤት የገባውን ወርቅ ቍጠር።
1 ዜና መዋዕል 15:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በራክያና ሕልቃናም ለታቦቷ በረኞች ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በራክያና ሕልቃና የታቦቱ በር ጠባቂዎች ነበሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በራክያና ሕልቃናም የታቦቱን እልፍኝ ጠባቂዎች ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በራክያ፥ ኤልቃና፥ ዖቤድኤዶምና ዩሒያ የቃል ኪዳኑ ታቦት ጠባቂዎች ሆነው ተመረጡ፤ ካህናቱ ሸባንያ፥ ኢዮሣፍጥ፥ ናትናኤል፥ ዐማሣይ፥ ዘካርያስ፥ በናያና ኤሊዔዘር በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ፊት እየሄዱ እምቢልታ እንዲነፉ ተመረጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በራክያና ሕልቃናም ለታቦቱ በረኞች ነበሩ። |
“ወደ ታላቁ ካህን ወደ ኬልቅዩ ወጥተህ ደጃፉን የሚጠብቁ ከሕዝቡ የሰበሰቡትን ወደ እግዚአብሔር ቤት የገባውን ወርቅ ቍጠር።
ገብተውም በከተማው በር ጮኹ፤ እንዲህም ብለው ተናገሩ፥ “ወደ ሶርያውያን ሰፈር ገባን፤ እነሆም፥ ፈረሶችና አህዮች ታስረው፥ ድንኳኖችም ተተክለው ነበር እንጂ ያገኘነው አልነበረም፤ የሰውም ድምፅ አልነበረም።”
ካህናቱም ሰበንያ፥ ኢዮሣፍጥ፥ ናትናኤል፥ ዓማሣይ፥ ዘካርያስ፥ በናያስ፥ አልዓዛርም በእግዚአብሔር ታቦት ፊት መለከት ይነፉ ነበር። አብዲዶምና ኢያኤያም የእግዚአብሔር ታቦት በረኞች ነበሩ።