ላባም ያዕቆብን፥ “በእውነት አንተ አጥንቴ ሥጋዬም ነህ፤ ከእኔ ጋር ተቀመጥ” አለው። አንድ ወር የሚያህልም ከእርሱ ጋር ተቀመጠ።
1 ዜና መዋዕል 11:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስራኤልም ሁሉ በኬብሮን ወደ ዳዊት ተሰብስበው እንዲህ አሉት፥ “እነሆ፥ እኛ የአጥንትህ ፍላጭ የሥጋህ ቍራጭ ነን፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤል ሁሉ በኬብሮን ወደ ዳዊት ተሰብስበው እንዲህ አሉ፤ “እነሆ፤ እኛ የዐጥንትህ ፍላጭ፣ የሥጋህ ቍራጭ ነን፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤልም ሁሉ በኬብሮን ወደ ዳዊት ተሰብስበው እንዲህ አሉት፦ “እነሆ፥ እኛ የአጥንትህ ፍላጭ የሥጋህ ቁራጭ ነን፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያን ሁሉ በኬብሮን ወደነበረው ወደ ዳዊት ሄደው እንዲህ አሉት፦ “እኛ ሁላችን የሥጋ ዘመዶችህ ነን፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስራኤልም ሁሉ በኬብሮን ወደ ዳዊት ተሰብስበው “እነሆ፥ እኛ የአጥንትህ ፍላጭ የሥጋህ ቍራጭ ነን፤ |
ላባም ያዕቆብን፥ “በእውነት አንተ አጥንቴ ሥጋዬም ነህ፤ ከእኔ ጋር ተቀመጥ” አለው። አንድ ወር የሚያህልም ከእርሱ ጋር ተቀመጠ።
አቤሴሎምም፥ “የመለከት ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ፥ አቤሴሎም በኬብሮን ነገሠ” በሉ የሚሉ ጕበኞችን ወደ እስራኤል ነገድ ሁሉ ላከ።
ከዚያም በኋላ ዳዊት፥ “ከይሁዳ ከተሞች ወደ አንዲቱ ልውጣን?” ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም፥ “ውጣ” አለው። ዳዊትም፥ “ወዴት ልውጣ?” አለ። እርሱም፥ “ወደ ኬብሮን ውጣ” አለው።
ዳዊትም በእስራኤል ላይ የነገሠበት ዘመን አርባ ዓመት ነበረ። በኬብሮን ሰባት ዓመት፥ በኢየሩሳሌምም ሠላሳ ሦስት ዓመት ነገሠ።
ወደ ምድረ በዳም ወጡ፤ ወደ ኬብሮንም ደረሱ፤ በዚያም የዔናቅ ዘሮች አኪማን፥ ሴሲ፥ ተላሚ ነበሩ። ኬብሮንም በግብፅ ካለችው ከጣኔዎስ ከተማ በፊት ሰባት ዓመታት ተሠርታ ነበር።
ከወንድሞችህ መካከል አምላክህ እግዚአብሔር የመረጠውን ለአንተ አለቃ ትሾማለህ፤ ወንድምህ ያልሆነውን ሌላ ሰው በአንተ ላይ መሾም አትችልም።
“ለሰቂማ ሰዎች ሁሉ፦ ሰባ የሆኑት የይሩበኣል ልጆች ሁሉ ቢገዙአችሁ ወይስ አንድ ሰው ቢገዛችሁ ምን ይሻላችኋል? ብላችሁ ንገሩአቸው፤ ደግሞም እኔ የአጥንታችሁ ፍላጭ፥ የሥጋችሁ ቍራጭ እንደ ሆንሁ አስቡ።”