ዔሳው ወደ ይስማኤል ሄደ፤ ቤሴሞትንም በፊት ካሉ ሚስቶቹ ጋር ሚስት ትሆነው ዘንድ ወሰዳት፤ እርስዋም የናኮር ወንድም የአብርሃም ልጅ የሆነው የይስማኤል ልጅና የናቡዓት እኅት ናት።
1 ዜና መዋዕል 1:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትውልዳቸውም እንደዚህ ነው። የይስማኤል በኵር ልጅ ናቢዎት፤ ቄዳር፥ ቢዲሄል፥ ሙባሳን፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዘሮቻቸው እነዚህ ናቸው፤ የእስማኤል በኵር ልጅ ነባዮት፣ ቄዳር፣ ነብዳኤል፣ መብሳም፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ትውልዳቸውም እንደዚህ ነው። የእስማኤል በኩር ልጅ ነባዮት፤ ከዚህ በኋላ ቄዳር፥ አድብኤል፥ ሚብሣም፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስማኤል ልጆች በእስማኤል በኵር ልጅ ስም የተጠራው ነባዮት፥ ቄዳር፥ አድበኤል፥ ሚብሣም፥ ሚሽማዕ፥ ዱማ፥ ማሣ፥ ሐዳድ፥ ቴማ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትውልዳቸውም እንደዚህ ነው፤ የእስማኤል በኵር ልጅ ነባዮት፤ ከዚህ በኋላ ቄዳር፥ ነብዳኤል፥ መብሳም፥ |
ዔሳው ወደ ይስማኤል ሄደ፤ ቤሴሞትንም በፊት ካሉ ሚስቶቹ ጋር ሚስት ትሆነው ዘንድ ወሰዳት፤ እርስዋም የናኮር ወንድም የአብርሃም ልጅ የሆነው የይስማኤል ልጅና የናቡዓት እኅት ናት።
እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ እኔ ጥቁር ነኝ፤ ነገር ግን ውብ ነኝ፥ እንደ ቄዳር ድንኳኖች እንደ ሰሎሞንም መጋረጃዎች።
ከቀስተኞች ቍጥር የቀሩት፥ የቄዳር ልጆች ኀያላን፥ ያንሳሉ፤” የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአልና።
የቄዳር በጎች ሁሉ ወደ አንቺ ይሰበሰባሉ፤ የነባዮትም አውራ በጎች ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ በመሠዊያዬ ላይም የተመረጠው መሥዋዕት ይቀርባል፤ የጸሎቴ ቤትም ይከብራል።