መዝሙር 94:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ሕዝብህን አደቀቁ፤ ርስትህንም አስጨነቁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ ሕዝብህን ረገጡ፥ ርስትህንም ጨቆኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! ሕዝብህን ያደቃሉ፤ የአንተን ወገኖች ይጨቊናሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባሕር የእርሱ ናትና፥ እርሱም ፈጥሯታልና። የብስንም በእጁ ፈጥሯታልና። |
“አሁን እዚህ ምን አለኝ?” ይላል እግዚአብሔር፤ “ሕዝቤ ያለ ምክንያት ተወስዷል፤ የገዟቸው ተሣልቀውባቸዋል” ይላል እግዚአብሔር። “ቀኑን ሙሉ፣ ስሜ ያለ ማቋረጥ ይሰደባል።
“እናንተ ርስቴን የበዘበዛችሁ ሆይ፤ ደስ ስላላችሁና ሐሤትም ስላደረጋችሁ፣ በመስክ እንዳለች ጊደር ስለ ፈነጫችሁ፤ እንደ ድንጉላ ፈረስ ስለ አሽካካችሁ፤
“የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በላን፣ አድቅቆ ፈጨን፤ እንደ ባዶ ማድጋ አደረገን፤ እንደ ዘንዶ ዋጠን፣ እንደ ጣፋጭ በልቶን ሆዱን ሞላ፤ በኋላም አንቅሮ ተፋን፤