Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 94:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እግዚአብሔር ሆይ! ሕዝብህን ያደቃሉ፤ የአንተን ወገኖች ይጨቊናሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 እግዚአብሔር ሆይ፤ ሕዝብህን አደቀቁ፤ ርስትህንም አስጨነቁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 አቤቱ፥ ሕዝብህን ረገጡ፥ ርስትህንም ጨቆኑ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ባሕር የእ​ርሱ ናትና፥ እር​ሱም ፈጥ​ሯ​ታ​ልና። የብ​ስ​ንም በእጁ ፈጥ​ሯ​ታ​ልና።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 94:5
20 Referencias Cruzadas  

የሕዝቤን ቅስም ልትሰብሩና ድኾችንም ልትበዘብዙ መብት የላችሁም፤ ይህን የተናገርኩ እኔ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ነኝ።”


ያቺ ሴት በቅዱሳን ደምና በኢየሱስ ሰማዕታት ደም ሰክራ አየኋት፤ ባየኋትም ጊዜ እጅግ በጣም ተደነቅሁ።


ሁለቱ ምስክሮቼ የሐዘን ልብስ ለብሰው አንድ ሺህ ሁለት መቶ ሥልሳ ቀን ትንቢት እንዲናገሩ ኀይል እሰጣቸዋለሁ።”


የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ኢየሩሳሌምን በዘበዘ አደቀቃትም እንደ ባዶ ዕቃም አደረጋት፤ እንደ ዘንዶ ሕዝብዋን ዋጠ፤ ምርጥ ምርጡን ወስዶ የቀሩትን እንደሚተፋ ምግብ ጣላቸው።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የባቢሎን ሕዝብ ሆይ! ሕዝቤን፥ በመበዝበዛችሁ ደስታና ሐሴት በማድረግ ፈንጥዛችሁ ነበር፤ በመስክ ላይ እንደምትፈነጭ ጊደር ተቀናጥታችሁ፥ እንደ ሰንጋ ፈረሶችም አሽካክታችሁ ነበር፤


የአንተ ሥራ ንጹሕ ደምን ማፍሰስና ሰውን መጨቈን ነው፤ ዐይንህና ልብህም የሚያተኲሩት አጭበርብሮ ትርፍን በማግበስበስ ላይ ብቻ ነው።


“ሕዝቤ ያለ ዋጋ ሲወሰድ እያየሁ አሁን እኔ የማደርገው ምን አለ? ገዢዎቻቸውም ይሳለቁባቸዋል፤ ያለማቋረጥም ስሜን ይሰድባሉ።


ይህንንም የምታደርገው እነርሱ ሕዝቦችህን ስለ ገደሉና ርስታቸውን ስለ አወደሙ ነው።


እነርሱም “ኑ በሥልጣናችን ሥር እናድርጋቸው” አሉ። በሀገሪቱ ያሉትን የተቀደሱ ቦታዎችን ሁሉ አቃጠሉ።


ነገር ግን ስለ አንተ በየቀኑ እንገደላለን፤ እንደሚታረዱ በጎችም ተቈጥረናል።


“እግዚአብሔር ክፉ አድራጊዎች ከቶ አያስተውሉምን? ሰዎች እንጀራን እንደሚበሉ ክፉ አድራጊዎች ሕዝቤን ይበዘብዛሉ፤ እነርሱም ወደ እኔ ወደ እግዚአብሔር አይጸልዩም።” ይላል።


ካላዳንከኝ ግን እንደ አንበሳ ነጥቀው ማንም ሊታደገኝ ወደማይችል ስፍራ ይወስዱኛል፤ ሰባብረውም ያደቁኛል።


የአንድ ሰው ጉዳይ ፍትሕ በሚያጣበት ጊዜ በውኑ ጌታ እነዚህን ነገሮች አያይምን?


በውስጥሽም አባትና እናት ይናቃሉ፤ የውጪ አገር ሰዎች ይታለላሉ፤ ባሎቻቸው የሞቱባቸው ሴቶችና አባትና እናት የሌላቸው ልጆች ይበደላሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios