ሰዎቹ ቀስተኞች ሲሆኑ፣ በቀኝም ሆነ በግራ እጃቸው ፍላጻ መወርወርና ድንጋይ መወንጨፍ የሚችሉ ነበሩ፤ እነርሱም ከብንያም ነገድ የሆነው የሳኦል ሥጋ ዘመዶች ነበሩ፤
መዝሙር 78:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኤፍሬም ልጆች የታጠቁ ቀስተኞች ቢሆኑም፣ በጦርነት ቀን ወደ ኋላ ተመለሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የኤፍሬም ልጆች ለውጊያ ታጥቀው ቀስትንም ገትረው በጦርነት ቀን ወደ ኋላ ተመለሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኤፍሬም ልጆች ቀስትና ፍላጻ ይዘው ሳለ በጦርነት ቀን ሸሹ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላካችንና መድኀኒታችን ሆይ፥ ርዳን፥ ስለ ስምህ ክብር አቤቱ፥ ታደገን፥ ስለ ስምህም ኀጢአታችንን አስተስርይልን። |
ሰዎቹ ቀስተኞች ሲሆኑ፣ በቀኝም ሆነ በግራ እጃቸው ፍላጻ መወርወርና ድንጋይ መወንጨፍ የሚችሉ ነበሩ፤ እነርሱም ከብንያም ነገድ የሆነው የሳኦል ሥጋ ዘመዶች ነበሩ፤
እስራኤላውያንም ይህን ሲያዩ ወዲያውኑ እንዲያፈገፍጉ ተስማሙ። ብንያማውያንን ማጥቃት እንደ ጀመሩ፣ ሠላሳ እስራኤላውያንን ስለ ገደሉ፣ “እንደ መጀመሪያው የጦርነት ጊዜ እያሸነፍናቸው ነው” አሉ።
የአቤድ ልጅ ገዓል እንዲህ አለ፤ “እንገዛለት ዘንድ አቢሜሌክ ማን ነው? ሴኬምስ ምንድን ናት? እርሱ የይሩባኣል ልጅ አይደለምን? ዜቡልስ የርሱ ረዳት ሹም አይደለምን? ለሴኬም አባት ለኤሞር ሰዎች ተገዙ፤ ለምን ለአቢሜሌክ እንገዛለን?
ስለዚህ ፍልስጥኤማውያን ተዋጉ፤ እስራኤላውያንም ስለ ተሸነፉ እያንዳንዱ ወደየድንኳኑ ሸሸ። ታላቅ ዕልቂት ሆነ፤ ከእስራኤልም ሠላሳ ሺሕ እግረኛ ወታደሮች ወደቁ።