La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 78:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እጅግ የተመኙትን ምግብ በመጠየቅ፣ እግዚአብሔርን በልባቸው ተፈታተኑት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የተመኙትን መብል እየጠየቁ፥ እግዚአብሔርን በልባቸው ፈተኑት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የተመኙትን ምግብ በመጠየቅ ሆን ብለው እግዚአብሔርን ተፈታተኑት።

Ver Capítulo



መዝሙር 78:18
10 Referencias Cruzadas  

ሥራዬን ቢያዩም፣ አባቶቻችሁ በዚያ ፈተኑኝ፤ ተፈታተኑኝም።


ስለዚህ፣ “የምንጠጣውን ውሃ ስጠን” በማለት ሙሴን ተጣሉት። ሙሴም፣ “እኔን ለምን ትጣሉኛላችሁ? እግዚአብሔርንስ ለምን ትፈታተኑታላችሁ?” አለ።


ስፍራውንም ማሳህና መሪባ ብሎ ጠራው፤ እስራኤላውያን ጠብ ፈጥረው፣ “እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ነው ወይስ አይደለም” በማለት እግዚአብሔርን ተፈታትነዋልና።


ድብልቁ ሕዝብ ሌላ ምግብ ጐመጀ፤ እስራኤላውያንም እንዲህ እያሉ ያጕረመርሙ ጀመር፤ “ምነው የምንበላው ሥጋ ባገኘን ኖሮ!


እነርሱ ክፉ እንደ ተመኙ፣ እኛም ደግሞ እንዳንመኝ እነዚህ ነገሮች ምሳሌ ሆነውልናል።


ከእነርሱ አንዳንዶቹ ጌታን እንደ ተፈታተኑና በእባብ ተነድፈው እንደ ጠፉ፣ እኛም ጌታን አንፈታተን።


በማሳህ እንዳደረግኸው እግዚአብሔር አምላክህን አትፈታተነው።