መዝሙር 68:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጢስ እንደሚበንን፣ እንዲሁ አብንናቸው። ሰም በእሳት ፊት እንደሚቀልጥ፣ ክፉዎችም እንዲሁ ከእግዚአብሔር ፊት ይጥፉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔር ይነሣ፥ ጠላቶቹም ይበተኑ፥ የሚጠሉትም ከፊቱ ይሽሹ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጢስ በነፋስ በኖ እንደሚጠፋ አብንናቸው፤ ሰም በእሳት ቀልጦ እንደሚያልቅ ክፉዎችም ከእግዚአብሔር ፊት ይጥፉ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጥልቅ ረግረግ ጠለቅሁ ኀይልም የለኝም፤ ወደ ጥልቁ ባሕርም ደረስሁ ማዕበሉም አሰጠመኝ። |
ሶርያውያንም ለጦርነት ተሰልፈው ዳዊትን በግንባር ገጠሙት፤ ይሁን እንጂ ከእስራኤል ፊት ሸሹ፤ ዳዊትም ሰባት መቶ ሠረገለኞችንና አርባ ሺሕ እግረኛ ወታደሮች ገደለባቸው። እንዲሁም የሰራዊታቸውን አዛዥ ሶባክን አቍስሎት ስለ ነበር፣ እዚያው ሞተ።
እሳት ሲለኰስ ጭራሮን እንደሚያቀጣጥል፣ ውሃንም እንደሚያፈላ፣ ስምህ በጠላቶችህ ዘንድ እንዲታወቅ ውረድ፤ መንግሥታትም በፊትህ እንዲንቀጠቀጡ አድርግ!
እንግዲህ ርኩሰት እንደ እሳት ይቀጣጠላል፤ እሾኽንና ኵርንችትን ይበላል፤ ጥቅጥቅ ያለውን ደን ያነድዳል፤ ጢሱም ተትጐልጕሎ እንደ ዐምድ ይቆማል።