Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 68:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እግዚአብሔር ይነሣ፤ ጠላቶቹ ይበተኑ፤ የሚጠሉትም ከፊቱ ይሽሹ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት የምስጋና መዝሙር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እግዚአብሔር ይነሣ! ጠላቶቹም ይበተኑ! የሚጠሉትም ከፊቱ ይሽሹ!

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 አቤቱ፥ ውኃ እስከ ነፍሴ ደር​ሶ​ብ​ኛ​ልና አድ​ነኝ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 68:1
21 Referencias Cruzadas  

ታቦቱ ለጕዞ በተነሣ ጊዜ ሁሉ ሙሴ፣ “እግዚአብሔር ሆይ፤ ተነሥ! ጠላቶችህ ይበተኑ፤ የሚጠሉህም ከፊትህ ይሽሹ” ይል ነበር።


ተነሥና እርዳን! ስለ ምሕረትህ ስትል ተቤዠን።


አንተ ረዓብን የተሰየፈ ያህል አደቀቅኸው፤ በብርቱ ክንድህም ጠላቶችህን በተንሃቸው።


ሕዝቦች በድምፅህ ነጐድጓድ ይሸሻሉ፤ መንግሥታት ስትነሣ ይበተናሉ።


“አሁንም እግዚአብሔር አምላክ ሆይ ተነሥ፣ ከኀይልህ ታቦት ጋራ ወደ ማረፊያ ቦታህ ግባ። እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፤ ካህናትህ ድነትን ይልበሱ፤ ቅዱሳንህም በቸርነትህ ደስ ይበላቸው።


በሸንበቆ መካከል ያሉትን አራዊት፣ በሕዝቡ ጥጆች መካከል ያለውንም የኰርማ መንጋ ገሥጽ፤ ብር ይገብር ዘንድም ይንበርከክ፤ ጦርነትን የሚወድዱ ሕዝቦችንም በትናቸው።


ሁሉን ቻዩ በዚያ የነበሩትን ነገሥታት በበተነ ጊዜ፣ በሰልሞን እንደሚወርድ በረዶ አደረጋቸው።


ጋሻችን ጌታ ሆይ፤ አትግደላቸው፤ አለዚያ ሕዝቤ ይረሳል፤ በኀይልህ አንከራትታቸው፤ ዝቅ ዝቅም አድርጋቸው።


እጅህ ጠላቶችህን ሁሉ ታገኛቸዋለች፤ ቀኝ እጅህም የሚጠሉህን ፈልጋ ትይዛለች።


ነገር ግን፣ የሚጠሉትን ዐይናቸው እያየ ይበቀላቸዋል፤ የሚጠሉትን ዐይናቸው እያየ ለመበቀል አይዘገይም።


አትስገድላቸው ወይም አታምልካቸውም፤ እኔ አምላክህ እግዚአብሔር የሚጠሉኝን ስለ አባቶቻቸው ኀጢአት እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድ ድረስ ልጆቻቸውን የምቀጣ ቀናተኛ አምላክ ነኝ፤


ወዲያውኑም ብረቱ፣ ሸክላው፣ ናሱ፣ ብሩና ወርቁ ተሰባበሩ፤ በበጋ ወራት በዐውድማ ላይ እንደሚገኝ እብቅም ሆኑ፤ ነፋስም አንዳች ሳያስቀር ጠራረጋቸው፤ ምስሉን የመታው ድንጋይ ግን ታላቅ ተራራ ሆነ፤ ምድርንም ሞላ።


የከበባው ጊዜ ሲፈጸም የጠጕሩን ሢሶ በከተማው ውስጥ አቃጥለው፤ ሌላውን ሢሶ ጠጕር በከተማዪቱ ዙሪያ ሁሉ በሰይፍ ቈራርጠው፤ የቀረውንም ሢሶ ደግሞ ለነፋስ በትነው፤ እኔም በተመዘዘ ሰይፍ አሳድዳቸዋለሁና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios