Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 22:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 እንደ ውሃ ፈሰስሁ፤ ዐጥንቶቼም ሁሉ ከመጋጠሚያቸው ወለቁ፤ ልቤ እንደ ሰም ሆነ፤ በውስጤም ቀለጠ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 እንደ ነጣቂና እንደሚያገሣ አንበሳ በላዬ አፋቸውን ከፈቱ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ጒልበቴ ደክሞ እንደ ውሃ ፈሰሰ፤ አጥንቶቼ ሁሉ ከመገጣጠሚያቸው ተለያዩ፤ ልቤም እንደ ሰም በውስጤ ቀለጠ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 22:14
15 Referencias Cruzadas  

በዚያ ጊዜ ንጉሡ በድንጋጤ ተሞላ፤ ፊቱም ተለዋወጠ፤ እጆቹና እግሮቹ ከዱት፤ ጕልበቶቹም ተብረከረኩ።


ሕይወቴ በመጨነቅ፣ ዕድሜዬም በመቃተት ዐለቀ፤ ከመከራዬ የተነሣ ጕልበት ከዳኝ፤ ዐጥንቴም በውስጤ ሟሟ።


እግዚአብሔር ልቤን አባባው፤ ሁሉን ቻይ አምላክ አስደነገጠኝ።


የጋይም ሰዎች እስራኤላውያንንም ከከተማዪቱ ቅጥር በር ጀምሮ እስከ ሽባሪም ድረስ በማባረር ቍልቍለቱ ላይ መቷቸው፤ ከእነርሱም ሠላሳ ስድስት ያህል ሰው ገደሉባቸው። ከዚህ የተነሣም የሕዝቡ ልብ ቀለጠ፤ እንደ ውሃም ፈሰሰ።


“አሁንስ ነፍሴ ተጨነቀች፤ ምን ልበል? አባት ሆይ፤ ከዚህች ሰዓት ብታድነኝስ? ይሁን፤ የመጣሁት ለዚህች ሰዓት ነውና።


ተበዝብዛለች፤ ተዘርፋለች፤ ተራቍታለች። ልብ ቀልጧል፤ ጕልበት ተብረክርኳል፤ ሰውነት ተንቀጥቅጧል፤ ፊት ሁሉ ገርጥቷል።


ጢስ እንደሚበንን፣ እንዲሁ አብንናቸው። ሰም በእሳት ፊት እንደሚቀልጥ፣ ክፉዎችም እንዲሁ ከእግዚአብሔር ፊት ይጥፉ።


ዐጥንቶቼን ሁሉ አንድ በአንድ መቍጠር እችላለሁ፤ እነርሱም አፍጥጠው ይመለከቱኛል።


“አሁን ነፍሴ በውስጤ ዐለቀች፤ የመከራ ዘመንም ይዞኛል።


እጅግ ተጨንቆም በብርቱ ይጸልይ ነበር፤ ላቡም እንደ ደም ነጠብጣብ ወደ ምድር ይፈስስ ነበር።


ከዚያም፣ “ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ እጅግ ዐዝናለች፤ እዚሁ ሁኑና ከእኔ ጋራ ነቅታችሁ ቈዩ” አላቸው።


ሰዎች በፌዝ አፋቸውን ከፈቱብኝ፤ በንቀት ጕንጬን ጠፈጠፉኝ፤ በአንድነትም በላዬ ተሰበሰቡ።


አፋቸውን አስፍተው ከፈቱብኝ፤ “ዕሠይ! ዕሠይ! በዐይናችን አየነው” አሉ።


“ጠላቶቻችን ሁሉ፣ አፋቸውን በእኛ ላይ ከፈቱ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios